የትምህርት ስርዓት

ስዊዘርላንድ ውስጥ መማናቸውም ግዜ ትምህርት መማር እና በግል ዕውቀትን ማዳበር ይቻላል። በተለይ የሙያ ስልጠና ማድረግ በጣም ጠቃሚ ነው። የሙያ ስልጠና የሚያደርግ ሰው፣ ስልጠናውን ሲጨርስ ሌላ ቀጣይ ስልጠና ወይም ዩንቨርስቲ መቀጠል ይችላል።

ተከታታይ ትምህርት / ኃላፊነቶች

ስዊዘርላንድ ውስጥ ተከታታይ የሆኑ ሶስት የትምህርት ደረጃዎች አሉ።

  • የግዴታ ትምህርት ቤት (Volksschule: Kindergarten, Primarschule und Sekundarstufe I)
  • መሰረታዊ የሙያ ትምህርት ወይም መካከለኛ ትምህርት (Sekundarstufe II)
  • ከፍተኛ የሙያ ዩንቨርስቲ / መደበኛ ዩንቨርስቲዎች እና ከፍተኛ የሙያ ትምህርት ቤቶች (Tertiärstufe)

መንግስታዊ /ህዝባዊ/ ማዕከላት ለሙያ ትምህርት በበላይነት ይቆጣጠራሉ። በፌደሬሽን፣ በካንቶን እና በኮምዩኖች ደረጃ ተግባርና ሃላፊነቱን ይጋራሉ። በየካንቶኖቹ የተለያየ ዓይነት ትምህርት ቤቶች እና የትምህርት ስርዓቶች ያሉት በዚህ ምክንያት ነው።

የመማር ግዴታ

በ Basel-Stadt ካንቶን የግዴታ ትምህርት 11 ዓመት ይወስዳል። ይህም ማለት፣ ተማሪዎች የግድ 11 ዓመት መማር አለባቸው። ልጅ ትምህርት የሚጀምረው 1 ዓመት ዕድሜ ሲሞላው ነው። ልጅዎ ትምህርት ቤት መሄድ ካልቻለ፣ ለልጅዎ ት/ቤት ይቅርታ መጠየቅ አለብዎት። ልጆች ይቅርታ ሳይጠቁ ከትምህርት ቤት ቢቀሩ፣ ወላጆች ሊቀጡ ይችላሉ።

ልጆች ዕድሚያቸው 16 ዓመት ከመሙላታቸው በፊት ወደ ባዝል ከተማ አዲስ ከመጡ፣ የግዴታ ትምህርት ቤት መማር ይፈቀላቸዋል። ነገር ግን ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ የሆኑ ወጣቶች ወደ ባዝል ከተማ አዲስ ከመጡ፣ የሙያ ትምህርት መረጃ ማዕከል (Berufsinformationszentrum, BIZ) መማር ይችላሉ።. የሙያ ትምህርት መረጃ ማዕከሉ (BIZ) ወጣቶች የትኛውን ዓይነት ትምህርት እና የሙያ ስልጠና ማድረግ እንደሚችሉ መረጃዎችን ይሰጣል።

ከግዴታዊ ትምህርት በኋላ የሙያ ስልጠና

ወጣቶች ከግዴታዊ ትምህርት በኋላ የሙያ ስልጠና ያደርጋሉ። አብዛኛዎቹ ወጣቶች መሰረታዊ የሙያ ስልጠናን ይመርጣሉ። (የሙያ ትምህርት፣ Berufslehre). ከጊዜ በኋላ ቆይተው ከፍተኛ የሙያ ስልጠና ትምህርት (höhere Berufsbildung) ያደርጋሉ። ይህንን ስልጠና እየወሰዱ በጎን ወይም ከስልጠናው በኋላ የሙያ ባካሎሬት (Berufsmaturität) መውሰድ ይችላሉ። ከዚህ ትምህርት በኋላ ተግባራዊ የሳይንስ ዩንቨርስቲ (Fachhochschule) መቀጠል ይችላሉ። በግምት 20 በመቶ የሚሆኑት ወጣቶች በ2ኛ ደረጃ ት/ቤት አጠናቀው (2 ደረጃ /ቤት ባካሎሬት gymnasiale Maturität) ይወስዳሉ። ከማትሪክ ውጤት በኋላ መደበኛ ዩንቨርስቲ መግባት ይችላሉ።

ስኮላርሺፕ

በቂ ገንዘብ ለሌላቸው ሰዎች ቀጣይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ለመማር እና የሙያ ስልጠና ትምህርት ለማድረግ ስኮላርሺፕ (Stipendien) ይሰጣል። እነዚህ ተማሪዎች ከግዴታው ትምህርት ከጨረሱ በኋላ ለሙያ ስልጠና ትምህርት ገንዘብ ይሰጣቸዋል። ከሌላ ክልል የእና የመጡም ቢሆኑና Basel-Stadt ግን የሚኖሩ ከሆነ ስኮላርሺፕ ሊሰጣቸው ይችላል። ወሳኙ ግን ከየት አገር እንደመጡ እና ምን ያህል ግዜ ስዊዘርላንድ እንደኖሩ ነው። የካንቶን አስተዳደር ጽ/ቤት ከሙያ ስልጠና ስኮላርሺፕ ሰጪ ቢሮ (Amt für Ausbildungsbeiträge) ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።