ቆሻሻ ማስወገድ

ለቆሻሻ አወጋገድ የኮምዩኑ ማዘጋጃ ቤቶች ተጠያቂዎች ናቸው።. ለዚህም ነው እያንዳንዱ ኮምዩን የየራሱ ህግጋት ያለው። ቆሻሻን ለመለየት ትልቅ ዋጋ ይሰጥዋል፣ ለዚህም ነው ልዩ የመሰብሰቢያ ቦታዎች ያሉት።

ቆሻሻ መለያየት / እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል

ቆሻሻን መለያየት አካባቢን ለመጠበቅ እና ገንዘብን ለመቆጠብ ይረዳል።. እንደገና ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ወይም ለአካባቢ ብክለት ቆሻሻዎች (ወረቀት፣ ባትሪዎች፣ ጠርሙዝ፣ ካርቶን፣ አረንጓዴ ቆሻሻ፣ አሉሚኒየም፣ ብረት፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ ዘይት፣ ወዘተ) ልዩ የመሰብሰቢያ ቦታዎች ወይም ስብስቦች አሉ። እነዚህ ቆሻሻዎች ከቤት ውስጥ ቆሻሻ ጋር አብሮ መጣል የለባቸውም። እያንዳንዱ ማዘጋጃ ቤት የራሱ የሆነ ቆሻሻ የማስወገጃ ፕላን (Entsorgungsplan) ወይም የቆሻሻ ቀን መቁጠሪያ (Abfallkalender) አለው። ይህም በምዝገባ ወቅት አብሮ ይሰጥዎታል። የትኛው ቆሻሻ መቼ እና መቼ ሊወገድ እንደሚችል ይገልጻል። ለእዚህ ዓላማ ባልታሰቡ ቦታዎች ላይ ቆሻሻ ማቃጠል ወይም መጣል የተከለከለ ነው።. የፕላስቲክ ጠርሙሶች (PET ጠርሙሶች) እና ሌሎች ማሸጊያዎች በሁሉም የሽያጭ ቦታዎች ላይ ከክፍያ ነጻ ሊወገዱ ይችላሉ።.

የቆሻሻ ከረጢት/ የቆሻሻ መጣያ ምልክቶች

እንደገና ጥቅም ላይ ሊውል የማይችል ቆሻሻ (የቤት ውስጥ ቆሻሻ ፣ Hausmüll) በBasel ውስጥ ባሉ ምልክት ያላቸው የቆሻሻ መጣያ ከረጢቶች ውስጥ መጣል አለበት። በሪሄን እና ቤቲንገን በከረጢቶች ውስጥ እና ምልክት ያላቸው የቆሻሻ መጣያ ከረጢቶች መጣል አለበት። የማስወገጃ ክፍያው በከረጢቶች ወይም ምልክት ያላቸው የቆሻሻ መጣያ ከረጢቶች ዋጋ ውስጥ ተካትቷል። ከረጢቶቹ ወይም መለያዎቹ፣ ለምሳሌ በኮምዩኑ ውስጥ ባሉ የገበያ ማዕከሎች እና ሱቆች ወይም ከራሱ ከኮምዩኑ ማዘጋጃ ቤት ሊገዙ ይችላሉ። የቆሻሻ ከረጢቱ በሳምንቱ የተወሰኑ ቀናት በመንገድ ላይ (ወይም አልፎ አልፎ በሌላ የመሰብሰቢያ ቦታ) መቀመጥ አለበት። ቆሻሻውን በሌሎች ቀናት ውስጥ ማስቀመጥ አይፈቀድም።. ብዙ ቤተሰቦች በሚኖሩበት በአፓርትመንት ሕንፃዎች ውስጥ አንዳንድ ጊዜ ልዩ የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች አሉ።. ማናቸውም ጥያቄዎች ካሉዎት፣ የእርስዎ የመኖሪያ ማህበረሰብ ወይም ጎረቤቶች ሊረዱዎት ይችላሉ።

ልዩ አደገኛ ቆሻሻ

ልዩ አደገኛ ቆሻሻ (Sonderabfälle) በተለይ መርዞችን ስለያዘ ወይም ለአካባቢ ጎጂ ስለሆነ መወገድ አለበት። እነዚህም ለምሳሌ ቀለሞች፣ ኬሚካሎች፣ ባትሪዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሃይል ቆጣቢ አምፖሎች እና ጊዜ ያለፈባቸው መድሃኒቶችን ያካትታሉ። በማንኛውም ሁኔታ በቤት ውስጥ ቆሻሻ ውስጥ አብረው አይገቡም።. ብዙ ጊዜ ከተገዛበት ቦታ ሊወገድ ይችላል። አምራች እና ነጋዴዎች ይህንን ቆሻሻ ያለክፍያ የመመለስ ግዴታ አለባቸው።