አካል ጉዳተኝነት

ለረጅም ጊዜ መሥራት የማይችል ወይም በጤና ምክንያት በከፊል ብቻ ሥራ መሥራት የሚችል ማንኛውም ሰው፣ እንደ ሁኔታው ከአካል ጉዳት ኢንሹራንስ (IV) የገንዘብ ድጋፍ የማግኘት መብት አለው። IV ገንዘብን ብቻ አይደለም የሚከፍለው። ከሁሉም በላይ ለኢንሹራንስ ገቢዎቹ በተለይም ወደ ሙያዊ ህይወታቸው እንዲገቡ ወይም እንደገና ወደ ስራ ዓለም እንዲገቡ ተገቢውን ድጋፍ ይሰጣል።

የአካል ጉዳት ኢንሹራንስ

የአካል ጉዳት መድን ኢንሹራንስ (IV) የመንግስት ተቋም ነው። አብዛኛው አዋቂዎች ከዚህ ለመጠቀም መዋጮ መክፈል አለባቸው። ለዚህ ብዙ አዋቂዎች መዋጮ መክፈል አለባቸው። መዋጮዎቹ በቀጥታ ከሠራተኞች ከወርሃዊ ደመወዛቸው ይቀነሳል። አሠሪው ግማሹን ይከፍላል። በግል ሥራ የሚተዳደሩ ሰዎች ወይም ሥራ የሌላቸው ሰዎች መዋጮውን እንዴት መክፈል እንዳለባቸው ከካሳ ቢሮ (Ausgleichskasse) ጋር መጠየቅ አለባቸው።

የአካል ጉዳት ኢንሹራንስ ድጋፍ

ቢያንስ ለአንድ ዓመት በጤና ምክንያት (በአካል ወይም በአእምሮ) ፍጹም መሥራት የማይችሉ ወይም በከፊሉ ብቻ መስራት የሚችሉ፣ ከ IV ድጋፍ የማግኘት መብት አላቸው። IV ድጋፉን ልክ እንደ ወርሃዊ የጡረታ አበል ይከፍላል። ነገር ግን ይህ የሚሆነው፣ ኢንሹራንስ የገባው ሰው በአካል ጉዳቱ ምክንያት ከስራ ህይወት ጋር ሊዋሃድ በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ የሚገኝ ከሆነ ነው። IV የአካል ጉዳተኞች ተስማሚ ሥራ እንዲያገኙ ይደግፋል። ከ IV ድጋፍ ለማግኘት ለማካካሻ ጽ/ቤት (Ausgleichskasse) ማመልከት ያስፈልጋል።

ተጨማሪ አገልግሎቶች

ከ IV ድጋፍ ቢኖራቸውም ለመኖር ግን በጣም አነስተኛ ገንዘብ ያላቸው ሰዎች፣ እንደ ሁኔታው ተጨማሪ የገንዘብ ድጎማዎችን (Ergänzungsleistungen). የማግኘት መብት ይኖራቸዋል። ይህንን ድጎማ ለማግኘት ማህበራዊ ድጎማ ቢሮ ማመልከት አለባቸው። ተጨማሪ ጥቅማ ጥቅሞችን የማግኘት መብት ያለው ማን እንደሆነ በግልፅ ተቀምጧል። ተጨማሪ ጥቅማ ጥቅሞች የሚሸፈነው በግብር ከፋዮች ነው።