የመኖሪያ ፍቃድ መብት

በግል ምክር ማግኘት አስፈላጊ ነው! ከተጎጂዎች ምክር አገልግሎት ስጪ ማዕከላት (Opferhilfe) ጋር መነጋገር የመኖሪያ መብትን ወደ ማጣት አያመራም። ውይይቱ አስተማማኝ እና ሚስጥራዊ ነው። የተጎጂዎች ምክር አገልግሎት ስጪ ማዕከላት ስለ ውይይቱ ለማንም አይናገሩም።

በቤት ውስጥ አመጽ ምክንያት ከመለያየት በኋላ የመኖሪያ ፍቃድ መብት (DE)

አንድ ሰው በትዳር ላይ ተመስርቶ በስዊዘርላንድ ውስጥ የሚኖር ከሆነ እና የቤት ውስጥ ጥቃት ቢያጋጥመው፣ ይህ ሰው ከመለያየት በኋላም ቢሆን እንደ ሁኔታው ስዊዘርላንድ ውስጥ በቀጣይነት ሊኖር ይችላል። እያንዳንዱ ሁኔታ የተለየ ነው። ለዚህም ነው የምክር አገልግሎት ማግኘት አስፈላጊ የሚሆነው።

የተጎጂዎች ምክር አገልግሎት ስጪ ማዕከላት (Opferhilfe) ድጋፍ ሊሰጡ ይችላሉ። ስፔሻሊስቱ/ ባለሙያው/ በወቅቱ ያለውን የህግ ሁኔታ ያብራራል እና ለተጎጂው በቀጣይ ደረጃዎች ድጋፍ ይሰጣል። የምክር አገልግሎቱ ከክፍያ ነጻ አስተማማኝ እና ሚስጥራዊ ነው። አስተርጓሚም ሊቀርብ ይችላል።

ጥቃትን መዝግቦ መያዝ

ጥቃት እንደተፈፀመ ለማረጋገጥ የማስረጃ መኖር በጣም አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ፡ የጉዳት ማረጋገጫ ፎቶዎች፣ የዛቻ ወይም የጥቃት ስክሪን ሾት ምስሎች በኋትስ- አፕ፣ በፌስ-ቡክ እና ሌሎችም ማስረጃዎች ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ መቀመጥ አለባቸው። ለምሳሌ፣ በጓደኛ ቤት ወይም በሥራ ቦታ።

በተጓዳኝም አንዳንድ በአካባቢው የሚገኙ ሰዎች ስለ ጥቃቱ ቢያውቁ መልካም ነው። ለምሳሌ፣ ጓደኛ፣ የስራ፣ የሰፈር ወይም የትምህርት ቤት ሰው ቢያውቅ ጥሩ ነው።