ወላጅነት እና ቤተሰብ

ልጅ ያለው ማንኛውም ሰው በስዊዘርላንድ ውስጥ በልጆች እና በትምህርት አበል በገንዘብ ይደገፋል። በሥራ ላይ ያሉ ሴቶች ልጅ ሲወልዱ ቢያንስ ለ14 ሳምንታት የሚከፈል የወሊድ ፈቃድ የማግኘት መብት አላቸው።

የእናትነት የወሊድ አበል

በሥራ ላይ ያሉ ሴቶች ልጅ ሲወልዱ ቢያንስ ለ14 ሳምንታት የሚከፈል የእናትነት የወሊድ ፈቃድ (Mutterschaftsurlaub) የማግኘት መብት አላቸው። በዚህ ጊዜ ውስጥ ቢያንስ 80 በመቶ የደሞዛቸውውን 80 ፐርሰንት ይከፈላቸዋል። ሥራ የሌላቸው ሴቶች ወይም መሥራት የማይችሉ ሴቶች እነሱም መብት እንዳላቸው በካሳ ቢሮ መጠየቅ አለባቸው። ይህንን በሚመለከት ልዩ ደንቦች አሉ።. ከወሊድ በኋላ ባሉት በመጀመሪያዎቹ ስምንት ሳምንታት ውስጥ እናቶች እንዲሠሩ አይፈቀድላቸውም (የወላድ ደህንነት ጥበቃ፣ Mutterschutz).

የአባትነት የወሊድ ፈቃድ

አባቶች ከወሊድ በኋላ ለሁለት ሳምንታት የሚከፈል የአባትነት የወሊድ ፈቃድ (Vaterschaftsurlaub) የማግኘት መብት አላቸው። ከየእናትነት የወሊድ ፈቃድ ጋር ሲነጻጸር፣ የአባትነት ፈቃድ ከወሊድ ፈቃድ ተለዋዋጭ ነው፡- ሁሉንም በአንድ ጊዜ ወይም በተለያዩ ቀናት ውስጥ ማግኘት መውሰድ ይቻላል። ነገር ግን ህጻኑ ከተወለደ በስድስት ወር ውስጥ ብቻ ነው የሚቻለው።

የቤተሰብ አበል

ማንኛውም ልጅ ያለው ሰው ከቤተሰብ አበል (Familienzulagen) በገንዘብ ይደገፋል። ይህም እስከ 16 ዓመት ለሆኑ ህጻናት ልጆች፣ የልጅ አበል እና ለወጣቶች የሙያ ስልጠና ላይ ካሉ እስከ 25 ዓመት የስልጠና አበል ይከፈላቸዋል። ስራ ያላቸው ወላጆች (የግል ስራ የሚተዳደሩትን ጨምሮ) ወይም የማይሰሩ እና አነስተኛ ገንዘብ ያላቸው ወላጆች ይህ መብት አላቸው። ለሠራተኞች የቤተሰብ አበል በየወሩ ከደመወዙ ጋር አብሮ ይከፈላቸዋል። ስለ ቤተሰብ ድጎማ አበል ተጨማሪ መረጃ ከአሠሪው ወይም ከማህበራዊ ኢንሹራንስ ተቋም ማግኘት ይቻላል። የቤተሰብ አበል መጠን ከካንቶን ወደ ካንቶን ይለያያል።

የቤተሰብ ኪራይ ድጎማ

አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች የተወሰኑ ሁኔታዎችን ካሟሉ የቤተሰብ ኪራይ ድጎማ (Familienmietzinsbeiträge). የድጋፍ ክፍያ ማመልከት ይችላሉ። የክፍያው መጠን በቤተሰቡ ገቢ፣ ንብረት እና በኪራይ መጠን ላይ የተመሰረተ ነው።