የሕፃናት ልጆች እንክብካቤ

ብዙ አባቶች እና እናቶች ልጅ ወልደውም እንኳን ቢሆን ስራ ይሰራሉ። ለዚህም ነው በBasel-Stadt ካንቶን ውስጥ ለህጻናት እንክብካቤ ልዩ አቅርቦቶች ያሉት። አብዛኛዎቹ አቅርቦቶች ክፍያ ያስከፍላሉ።

የልጆች የቀን እንክብካቤ ማዕከላት

በልጆች የቀን እንክብካቤ ማዕከላት ልጅዎት ቀኑን ሙሉ እንክብካቤ ይደረግለታል። የልጆች የቀን እንክብካቤ ማዕከላት በምህጻረ -ቃል Kita ይባላሉ። ብዙዎቹ Kita‘ዎች ከ3 ወራት እስከ ለትምህርት የደረሱ ልጆች የሚውሉበት ነው። በተጨማሪም አንዳንድ Kita‘ዎች ትምህርት ለጀመሩ ሕጻናት ከትምህርት ቤት በፊት፣ በምሳ ሰዓት እንዲሁም ከትምህርት በኋላም ይንከባከባሉ።

ልጅዎን በጣም ቀደም ብለው ማስመዝገብ አለብዎት፣ አለበለዚያ ግን ወረፋው በጣም ረጅም ነው። የKita‘ዎች የክፍያ ዋጋ የተለያየ ነው። የሚኖሩበት ኮምዩን ለአንዳንድ Kita‘ዎች ወጪዎችን በከፊል ይሸፍናሉ። Kita‘ዎች እና የሚኖሩበትን ኮምዩን Kita ምን ያህል ወጪ እንደሚያስወጣ እና ልጅዎን እንዴት እንደሚያስመዘግቡ መጠየቅ ይችላሉ።

የጨዋታ ቡድኖች

ብዙ ልጆች ትምህርት ቤት ከመጀመራቸው በፊት የጨዋታ ቡድኖችን ይሳተፋሉ (Spielgruppe)። በጨዋታ ቡድን ውስጥ ከ3 ዓመት እድሜ ጀምሮ ያሉ ልጆች ያለ ወላጆቻቸው ተገናኝተው ይጫወታሉ።. በሙያ የሰለጠኑ ተንከባካቢዎች ልጆቹን ጨዋታ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ያግዟቸዋል። ልጆቹ መገጣጠም እና መጫወት ለምሳሌ አብረው በአንድ ላይ በመጫወቻ ቡድኑ ለመጫወት በፈቃደኝነት ነው። ልጅዎት ቤት ውስጥ ጀርመንኛ አይናገርም? እዚያም በጨዋታ ቡድን ውስጥ ጀርመንኛ መማር እንዲጀምር ጥሩ አጋጣሚ ነው። ይህም ልጅዎ ትምህርት ሲጀምር እንዲቀለው ያደርገዋል።

ዕለታዊ ፕሮግራሞች / ምሳ

በሁሉም የመጀመሪያ ደረጃዎች እና ሁለተኛ ደረጃዎች ውስጥ በትምህርት ቤት ሕንፃ ውስጥ ወይም በጣም ቅርብ አካባቢ. ዕለታዊ ፕሮግራሞች (Tagesstrukturen) ይካሄዳሉ። ዕለታዊ ፕሮግራሞች ማለት ልጆቹ በምሳ ሰአት ትምህርት ቤት ይቆያሉ እናም ምሳ ይሰጣቸዋል። ከት/ቤት በኋላ ልጆቹን የሚንከባከባቸው ሰው ይኖራል፣ እዛም ልጆቹ የቤት ስራቸውን ሊሰሩ ይችላሉ።.

በቀን ህጻን ተንከባካቢ ቤተሰቦች

ልጅዎን በቀን ህጻን ተንከባካቢ ቤተሰቦች እንክብካቤ እንዲደረግላቸው ማድረግ ይችላሉ። በቀን ህጻን ተንከባካቢ ቤተሰቦች (Tagesfamilie) ማለት እንደ ቤተሰብ ሆነው ቀኑን ሙሉ ልጅን የሚንከባከቡ ወይም ከትምህርት ቤት በኋላ ቤታቸው በመውሰድ ልጅን የሚንከባከቡ ናቸው። አገናኝ /አቅራቢ/ ቢሮዎች ለርሶ የሚስማማ የቀን ህጻን ተንከባካቢ ቤተሰብ በመፈለግ ይረዱዋችኋል። እነዚህ አገናኝ ቢሮዎች አንድ የቀን ህጻን ተንከባካቢ ቤተሰብ ምን ያህል እንደሚያስከፍሉ መረጃ ይሰጥዎታል።

የሕፃናት ተንከባካቢ / ድንገተኛ ሁኔታዎች

ስዊዘርላንድ በማታ ወይም በሳምንቱ መጨረሻ ወጣቶች የሕፃናትን የመንከባከብ ስራ ይሰራሉ። ወጣቶቹ ለስራውም ይከፈላቸዋል። የስዊዘርላንድ ቀይ መስቀል ማህበር Basel-Stadt (SRK) የሕፃናት ተንከባካቢ የሚያገናኙ አቅራቢ ቢሮዎች የስም ዝርዝር አለው። እነሱም የእንክብካቤ ኮርስ የወሰዱ ናቸው።

በድንገተኛ ሁኔታ ወቅት የሕጻናት እንክብካቤ፣
ምናልባት ድንገተኛ ሁኔታ ሊያጋጥም ይችላል እና እርስዎም በአስቸኳይ ልጅዎትን የሚንከባከብሎት ሰው ይፈልጉ ይሆናል። ለምሳሌ ያህል፣ እርስዎ ወይም አጋርዎ ሆስፒታል መሄድ ያስፈልጎት ይሆናል፣ ሆኖም ግን ልጅዎን የሚንከባከብሎት ሰው ላይኖር ይችላል። በዚህ ግዜ የስዊዘርላንድ ቀይ መስቀል ማህበር Basel-Stadt (SRK) በድንገተኛ ሁኔታ ወቅት የሕጻናት እንክብካቤ ያደርጋል። እንክብካቤውም በክፍያ ነው። ነገር ግን አንዳንድ የጤና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ወጪውን ይሸፍናሉ።