የግዴታ ት/ቤት

በግዴታ ትምህርት ቤት ውስጥ ልጆች መሠረታዊ ትምህርት ይቀበላሉ።. ከዚያ በኋላ ተጨማሪ ስልጠና ሊያደርጉ ይችላሉ።.የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ነፃ ናቸው።

ልጅን ማስመዝገብ

የሕዝብ /የመንግስት/ ትምህርት ቤቶችን የማስተዳደር ኃላፊነት ያላቸው የኮምዩን ማዘጋጃ ቤቶች ወይም ካንቶኖች ናቸው።

ልጅዎን እዚህ ያስመዝግቡት፡-

መዋዕለ ሕፃናት ወይም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ምዝገባ፣

  • በባዝል-ከተማ ላሉ ልጆች፡ ባዝል-ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች
  • በሪሄን ላሉ ልጆች፡ የሪሄን የኮሚዩን ትምህርት ቤት
  • በቤቲንገን ላሉ ልጆች፡ የማህበረሰብ ትምህርት ቤት ቤቲንገን።

ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምዝገባ፣

  • ባዝል-ከተማ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች

የትምህርት ቤት ደረጃዎች

የግዴታ ትምህርት ቤት 3 ደረጃዎች አሉት። ደረጃዎቹም ተከታታይ ናቸው።

  • መዋዕለ ሕፃናት (Kindergarten) ለ2 ዓመታት ይፈጃል፣.
  • የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት (Primarschule) ለ6 ዓመታት ይቆያል።. ልጅዎ ልዩ ድጋፍ ያስፈልገዋል ወይንስ ልዩ ችሎታዎች አሉት? ይህም ከሆነ እዚህ ትክክለኛውን ድጋፍ ያገኛል።
  • የላይኛው ደረጃ ትምህርት (Sekundarstufe I) ለ3 ዓመታት ይቆያል።. በላይኛው ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ሦስት የተለያዩ የትምህርት ዓይነቶች አሉ (A-Zug, E-Zug, P-Zug). የትምህርት ቤቶች ዓይነቶች የተለያየ ክብደት አላችው።
  • ጀርመንኛ የልጅዎ የአፍ መፍቻ ቋንቋ አይደለም? ከዚያም በሶስቱም ደረጃዎች ላይ ልዩ ድጋፍ ያገኛል።

ትምህርት በአፍ መፍቻ ቋንቋ- እና በራስ ባህል መማር (HSK)

ከግዳጅ ትምህርት በተጓዳኝ ልጆች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እና ባህላቸው (heimatliche Sprache und Kultur, HSK) ኮርሶች መከታተል ይችላሉ። ልጆቹ ቋንቋውን ይማራሉ እና በተሻለ ሁኔታ መረዳት፣ መናገር፣ ማንበብ እና መጻፍ ይማራሉ።. እና ስለትውልድ አገራቸው ታሪክ ፣ ጂኦግራፊ ፣ በዓላት እና ወጎች ያውቃሉ። እነዚህን ኮርሶች እንዲማሩ እንመክራለን።. በፈቃደኝነት የሚሰጡ ኮርሶች ናቸው እናም አብዛኛውን ጊዜ ገንዘብ ያስከፍላሉ.

የመንግስት / የግል ትምህርት ቤት

የሕዝብ/ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ነፃ ናቸው። ወንዶች እና ሴቶች ልጆች አንድ ላይ ትምህርት ይማራሉ። ትምህርቶቹ ከእምነት ገለልተኛ ናቸው።. አብዛኛዎቹ ልጆች እና ወጣቶች (95 ከመቶ) የሚሆኑት ለግዴታ ትምህርት ወደ የሕዝብ ትምህርት ቤት ይሄዳሉ። የግል ትምህርት ቤቶችም አሉ። ልጅዎን ወደ የግል ትምህርት ቤት ከላኩ፣ ለትምህርት ቤቱ በግልዎ መክፈል አለብዎት።.

የወላጆች መብት እና ግዴታዎች

ልጅዎ በትምህርት ቤት ምን እየሰራ እንደሆነ እና በትምህርት ቤት ውስጥ ምን ያህል አቋም ላይ እንዳለ ትምህርት ቤቱ ማሳወቅ አለበት። ለዚህም ነው ከእርስዎ እና ከመምህሩ ጋር ውይይቶች ያሉት።. በተጨማሪም መምህራን በትምህርት ቤት ልጅዎ ባለበት ክፍል ውስጥ ላሉ ወላጆች ሁሉ የሚያሳውቁባቸው የወላጆች ምሽቶችም አሉ። እና ስለ ትምህርት ቤቱ መረጃ ያላቸው ዝግጅቶች አሉ።. በእነዚህ ንግግሮች እና ዝግጅቶች ላይ መገኘት አለቦት። ልጅዎ በመደበኛነት ትምህርት ቤት እንዲከታተል የማረጋገጥ ሃላፊነት አለብዎት።

ምናልባት ልጅዎ ለንድ ጊዜ ትምህርት ቤት መሄድ አይችል ይሆናል፣ ለምሳሌ ታሞ ከሆነ።. ይህ ከሆነ ለትምህርት ቤቱ ማሳወቅ አለብዎት።. እንዲሁም ልጅዎ የቤት ስራውን መስራቱን ማረጋገጥ አለብዎት። በዚህ ልጅዎን መደገፍ ይችላሉ።. ለምሳሌ በትምህርት ቤት ምን እየሰራ እንደሆነ መጠየቅ ይችላሉ። እና የቤት ስራውን በመደበኛነት መመልከት ይችላሉ።በዚህም ፍላጎት እንዳለዎት ያሳያሉ።

ስለ ስዊዘርላንድ የትምህርት ስርዓት ጥሩ አድርገው ካላወቁ፣ በዝግጅቶች ላይ የበለጠ ማወቅ ይችላሉ። በተለይ ለስዊዘርላንድ አዲስ ለሆኑ ሰዎች የመረጃ ዝግጅቶች አሉ። ስለዚህ ዝግጅቶቹ ብዙውን ጊዜ በጀርመን ሳይሆን በሌሎች ቋንቋዎች ነው።.

ጥያቄዎች / እገዛ

ስለ ትምህርት ቤቱ ጥያቄ ካለዎት ሁል ጊዜ መምህሩን ማነጋገር አለብዎት። ድጋፍ ከፈለጉ መምህሩ ለእርስዎም ዝግጁ ነው። መምህሩ ምናልባት ልጅዎ የሆነ ነገር እንደሚያስፈልገው ሊሰማው ይችላል፣ ወይም መምህሩ ስለ ልጅዎ ጥያቄ ሊኖረው ይችላል።. ከዚያም መጀመሪያ ከርስዎ ጋር ይነጋገራል። ወላጆች እና አስተማሪዎች አብረው በደንብ ተጋግዘው ቢሰሩ በጣም ጠቃሚ ነው። ምናልባት ልጅዎ የአእምሮ ወይም የማህበራዊ ችግር ሊኖረው ይችላል።. የትምህርት ቤቱ ሳይኮሎጂካል አገልግሎት (Schulpsychologischer Dienst) እርስዎን እና ልጅዎን ይረዳል። እርዳታው ነፃ ነው።