ሕክምናዊ እንክብካቤ

በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች ማንኛውም ሰው የታመመ ወይም አደጋ ያጋጠመው እንደሆነ መጀመሪያ የቤተሰብ ዶክተር ማየት ይኖርበታል ። በጥቃቅን በሽታዎች ወይም በአደጋዎች ጊዜ በመድሃኒት ቤት ውስጥ እርዳታ ማግኘት ይችላሉ ። በጣም ከባድ በሆኑ ድንገተኛ ሁኔታዎች ውስጥ ብቻ በቀጥታ ወደ ሆስፒታል መሄድ አለብዎት።

መድሃኒት ቤቶች

መድሃኒት ቤቶቹ በሐኪም የታዘዙ መድሃኒቶች (ያለ ሃኪም ትዕዛዝ የማይገዙ) እና ሌሎች መድኃኒቶችን ይሸጣሉ። ቀላል ሕመም ካለብዎት በመጀመሪያ ወደ መድሃኒት ቤት እንዲሄዱ ይመከራል። ፋርማሲስቶቹ በደንብ የሰለጠኑ ናቸው እና ደንበኞቻቸውንም ያማክራሉ፣ በፔተርስግራበን 3 (Petersgraben 3 ) የሚገኘው የድንገተኛ መድሃኒት ቤት በሌሊት እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ክፍት ስለሆነ በድንገተኛ ጊዜ መድሃኒት ማግኘት ይችላሉ።

የቤተሰብ ዶክተር / የሕፃናት ሐኪም

በስዊዘርላንድ ብዙ ሰዎች የቤተሰብ ዶክተር (Hausarzt oder Hausärztin) አላቸው። ሃኪሞቹ የግል የሕክምና ታሪክን ያውቃሉ እና ለህክምና ችግሮች የመጀመሪያ የመገናኛ ተጠሪዎች ናቸው። ለልጆች የሕፃናት ሐኪሞች አሉ። አስፈላጊ ከሆነ ታካሚውን ወደ ልዩ ባለሙያ ሐኪም ወይም ወደ ሆስፒታል ይልካሉ ። ከባድ ድንገተኛ ሁኔታ ካጋጠመ ብቻ ነው ወደ ሆስፒታል በቀጥታ መሄድ ያለብዎት። ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች የህክምና ድንገተኛ የጥሪ ማእከል (Medizinische Notrufzentrale፣ MNZ) ከዶክተር ቢሮ የስራ ሰዓት ውጭ ይገኛል። ይህም በቀን 24 ሰዓት በ061 261 15 15 ደውለው በድንገተኛ አደጋ ውስጥ ላሉ ህፃናት እና ወጣቶች የህጻናት ህክምና አገልግሎት ከተከፈቱበት ሰዓት ውጪ የሜድጌት ኪድስ መስመር በክፍያ በሚደወል ስልክ ቁጥር 0900 11 44 ​​11 ማግኘት ይቻላል።

የጥርስ ሐኪም

የጥርስ ህክምናን ወጪ አብዛኛውን ጊዜ በግልዎ መከፈል አለብዎት። ሆኖም ግን የጥርስ ህክምናን የሚሸፍን ተጨማሪ ኢንሹራንስ የመግባት አማራጭ አለ። በትምህርት ገበታ የሚገኙ ልጆች፣ በዓመት አንድ ጊዜ ነጻ የጥርስ ምርመራ የማግኘት መብት አላቸው። ትምህርት ቤቱ በዚህ ላይ አስፈላጊ መረጃ ይሰጣል።

Krankenhaus / የአደጋ ጊዜ ጣቢያዎች (DE)

አንድ ሰው ወደ ሆስፒታል (Spital) መሄድ ካለበት፣ ብዙውን ጊዜ በዶክተር ይመዘገባል። አንድ ሰው በቀጥታ ወደ ሆስፒታል ድንገተኛ ጣቢያ መሄድ ያለበት ለየት ያለ ከባድ ድንገተኛ አደጋዎች ካጋጠሙት ብቻ ነው። ሁኔታው ለሕይወት አስጊ ከሆነ ወይም በሽተኛው ወደ ህክምና መወሰድ ካለበት የአደጋ ጊዜ ቁጥር 144 መደወል አለበት። ቀላል በሆኑ ድንገተኛ አደጋዎች አጠቃላይ ህክምናውን የሚመለከተው ሀኪሙ ነው።

እቤት ውስጥ መንከባከብ

ቤት ውስጥ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የታመሙ ሰዎች ወይም እንክብካቤ የሚፈልጉ ሰዎች የሆስፒታል ያልሆነ ነርሲንግ (Spitex) አገልግሎቶችን መጠቀም ይችላሉ። ስፔሻሊስቶች በሽተኞቹን ለመንከባከብ ወይም በቤቱ ውስጥ ለመርዳት ወደ ህሙማኑ ቤት ይሄዳሉ። ይህ አቅርቦት በህመም፣ በአደጋ፣ በእርጅና፣ በእርግዝና ወቅት ወይም ከወሊድ በኋላ በሚፈጠሩ ችግሮች ምክንያት በድጋፍ ላይ ጥገኛ ለሆኑ ሰዎች ነው። አንዳንድ ወጪዎች በመሠረታዊ ኢንሹራንስ (Grundversicherung) የተሸፈኑ ናቸው. ከSpitex Basel በተጨማሪ ብዙ የግል Spitex አቅራቢዎች አሉ።