ስራ አጥነት

ሁሉም ሰራተኞች ለስራ አጥነት ዋስትና ኢንሹራንስ አላቸው። ሥራ አጥ የሆኑ ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ በህጉ መሰረት የገንዘብ ድጋፍ ያገኛሉ። ሥራ የሌላቸው ሰዎች በክልል የቅጥር ማእከል (RAV) መመዝገብ አለባቸው። በስራ መፈለግም ይረዳቸዋል።.

የሥራ አጥነት ኢንሹራንስ

የስራ አጥነት መድን ኢንሹራንስ (ALV) የመንግስት ተቋም ሲሆን ለሁሉም ሰራተኞች አባል መሆን ግዴታ ነው። ወርሃዊ መዋጮ በቀጥታ ከደመወዝ ይቆረጣል፣ አሠሪው ግማሹን ይከፍላል። በግል ስራ የሚተዳደሩ ለሥራ አጥነት ዋስትና መድን አባል መሆን አይችሉም። ሥራ አጥ የሆነ ማንኛውም ሰው ከሥራ አጥ ኢንሹራንስ ፈንድ ወርሃዊ የደመወዝ ምትክ (የሥራ አጥ ድጎማ ክፍያ፣ Arbeitslosengeld) ይቀበላል። መቼ እና ምን ያህል የሥራ አጥነት ክፍያ/ድጎማ/ ማግኘት እንደሚቻል፣ በብዙ በተለያዩ መስፈርቶች ይወሰናል። ለምሳሌ ያህል ጊዜ ስራ እንደሰራና ወይም ስራ አጥ የሆነበት ምክንያት ይወስነዋል።

በስራ አጥነት ግዜ የሚወሰዱ እርምጃዎች

ከመጨረሻው የሥራ ቀን በፊት፣ ቢዘገይ ግን በመጀመሪያው የሥራ አጥነት ቀን፣ በሚመለከተው ክልላዊ የስራ የቅጥር ማእከል (Regionales Arbeitsvermittlungszentrum, RAV) በህጉ መመዝገብ ግዴታ ነው። እዚያም ሁሉም የሚያስፈልግ ቀጣይ ሂደቶች ገለጻ ይደረግሎታል።

ክልላዊ የስራ የቅጥር ማዕከል

ክልላዊ የስራ የቅጥር ማዕከል (RAV) ሌላ ሥራ በፍጥነት ማግኘት እንዲቻል ያግዛል። የስራ አጥነት ጥቅማጥቅም ከተቀበሉ በRAV ያሉት የምክር ቃለመጠይቆች ግዴታ ናቸው። RAV በተጨማሪም ኮርሶችን ወይም ለቅጥር የሚያግዙ ፕሮግራሞችን ይሰጣል። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ደግሞ አስገዳጅ ኮርሶች ናቸው።. በስዊዘርላንድ ውስጥ ሰርተው የማያውቁ እና ሥራ የሚፈልጉ ሰዎች እንኳን በ RAV መመዝገብ ይችላሉ። ግን ምንም ገንዘብ አይሰጣቸውም።