ግጭቶች

በቤተሰብ ወይም በጓደኞች መካከል ግጭት እና ጥል አለ? ካለ የተለያዩ የምክር አገልግሎት ሰጪ ጽ/ቤቶች በቀጣይነት ሊያግዝዎት ይችላሉ። በቤተሰብ ውስጥ እና በትዳር ጓደኛማቾች መካከል ጥቃት መፈጸም ክልክል ነው። "ሄሎ ባዝል ከተማ" ላይ የቤት ውስጥ ጥቃትን በሚመለከት ራሱን የቻለ አርእስት ተሰጥቶታል። እዛም ይህንን አርእስት በሚመለከት በቂ መረጃ ያገኛሉ።

በጓደኞች መካከል ግጭት

ከአጋርዎ ጋር ችግር ካለብዎት የሰለጠኑ ባለሙያዎች እርዳታ ማግኘት ይችላሉ። (የትዳር የምክር አገልግሎት ማዕከል፣ Eheberatung). መፍትሄዎችን ለማግኘት ከእርስዎ ጋር አብረው የሚሰሩ ልዩ የምክር አገልግሎት ማዕከላት አሉ። አብዛኛውን ግዜ የመጀመሪያው ንግግር ነጻ ነው፣ ወይም ትንሽ ነው የሚያስከፍለው።

በቤተሰብ መካከል ግጭት

ልጆች ካለዎት፣ አልፎ አልፎ ከባድ የሆኑ ሁኔታዎች ሊያጋጥሙ ይችላሉ። ይህም ለወላጆችና ለልጆች ውጥረት ይፈጥርባቸዋል። በቀጣይነት መፍትሔ ለማግኘት ከተቸገሩ እርዳታ መጠየቅ ከሁሉም የተሻለ ነው።

እርዳታ ለወላጆች፣

  • የቤተሰብ የምክር አገልግሎት ማዕከል (Familienberatungsstelle) በግልዎ የምክር አገልግሎት ያገኛሉ።
  • ስለ ልጅ አስተዳደግ ጥያቄዎች ካለዎት ወይም የልጆችዎ ሁኔታ የሚያሳስብዎት ከሆነ፣ የወላጆች ድንገተኛ ስልክ አገልግሎት ጥሪ ይጠቀሙ። በሰለጠኑ ባለሙያዎች የምክር አገልግሎት ያገኛሉ፣ በስልክ ቁጥር 0848 35 45 55 ይደውሉ /መደበኛ የቤት ስልክ ክፍያ ነው የሚከፍሉት/ ወይም ኢ-ሜይል ይጻፉ።

ለልጆችና ለወጣቶች፣

  • ልጆችና ወጣቶች የአደጋ ጊዜ ቁጥር መደወል ይችላሉ። ኢ-ሜይል ወይም የአጭር ጽሑፍ መልዕክት ይጻፉ፣ ወይም ቻት ያድርጉ። ቴለፎን 147 ይደውሉ (የነጻ ስልክ ነው).

የቤት ውስጥ ጥቃት

በቤተሰብ ውስጥ ጥቃት ኦፊሻል የሆነ ወንጀል ነው፣ በዚህም የተነሳ ክልክል ነው። አንድ ሰው ጥቃት ከፈጸመ፣ በወንጀል ተጠያቂ ይሆናል። ማንኛውም ዓይነት ጥቃት የተከለከለ ነው። ማንም ሰው በቤተሰቡ ውስጥ ባሉ ሌሎች ሰዎች፣ በትዳር አጋር ላይ ወይም በልጆች ላይ የኃይል እርምጃ መውሰድ አይችልም። ባለስልጣን ጽ/ቤቶች የቤት ውስጥ ጥቃት መፈጸሙን ካረጋገጡ፣ ወዲያውኑ እርምጃ መውሰድ አለባቸው።

ቤተስብ ውስጥ ጥቃት ይደርስብዎታል? እርዳታ የት ማግኘት እንደሚችሉ የሚጠቁሙ አቅርቦቶች አሉ። አቅርቦቶቹ ከክፍያ ነጻ ናቸው እናም በሚስጥርም የተጠበቁ ናቸው።

  • Frauenhaus / Väterhaus: ሴቶች ወይም ወንዶች ጥቃት በሚደርስባቸው ግዜ፣ ለተወሰነ ግዜ የሴቶች መጠለያ ወይም የወንዶች መጠለያ ውስጥ መኖር ይችላሉ። ከልጆችዎ ጋራ በአንድ ላይ ከለላ መፈለግ ይችላሉ። ሴቶች በሴቶች መጠለያ ቀንና ለሊት በስልክ ቁጥር 061 681 66 33 መደወል ይችላሉ።
  • የልጆች የአደጋ ጊዜ ጥሪ፣ ልጆችና ወጣቶች የአደጋ ጊዜ ቁጥር መደወል ይችላሉ። ቴለፎን 147 በነጻ መደወል ይችላሉ።
  • ከቤተሰብ አባላትዎ ውስጥ ከአንዳቸው ስጋት እንዳለዎት ይሰማዎታል? ከተሰማዎት በቴለፎን ቁጥር 117 ፖሊስ ይደውሉ። ፖሊስ ጥቃት ፈጻሚውን ከአፓርታማው ወይም ከቤቱ ረዘም ላለ ጊዜ ማስወጣት ይችላል። ጥቃት ፈጻሚው ወደ አፓርታማ ወይም ቤት ውስጥ እንዲገባ አይፈቀድለትም።

"ሄሎ ባዝል ከተማ" ላይ የቤት ውስጥ ጥቃትን በሚመለከት ራሱን የቻለ አርእስት ተሰጥቶታል። እዛም ይህንን አርእስት በሚመለከት በቂ መረጃ ያገኛሉ።