ክፍት የስራ ሰዓቶች / በዓላት

ከባቡር ጣቢያዎች ወይም ከነዳጅ ማደያዎች በስተቀር፣ በስዊዘርላንድ አብዛኛዎቹ ሱቆች እሁድ ዝግ ናቸው። ህዝባዊ በዓላት የሚወሰኑት በካንቶኖች ነው።

በዓላት

ህዝባዊ በዓላት በሰራተኛ ህግ ላይ የተደነገጉ ሲሆን በሕጉ መሰረት ልክ እንደ እሁድ የእረፍት ቀን ናቸው። ነሐሴ 1 (ብሄራዊ በዓል) በመላው ስዊዘርላንድ ህዝባዊ በዓል ነው። በተጨማሪም እያንዳንዱ ካንቶን ተጨማሪ ኦፊሻላዊ በዓላትን ማጽደቅ ይችላል። በካንቶን Basel-Stadt የሚከተሉት ቀናት በዓላት ናቸው። አዲስ አመት (ታህሳስ 1) ፣ ስግደት (ቅድመ ፋሲካ ዓርብ)፣ ፋሲካ፣ የሰራተኞች ቀን (ግንቦት 1) ፣ እርገት (ከፋሲካ ከ40 ቀን በኋላ ሐሙስ)፣ የመንፈስ ቅዱስ ቀን /ፊንግስተን/፣ ብሄራው በዓል (ነሐሴ 1)፣ ገና (ታህሳስ 25)፣ የእስጢፋኖስ ቀን (ታህሳስ 26).

የገበያ ሱቆች የሚከፈቱበት ሰዓት

የገበያ ሱቆች የመክፈቻ ሰዓታት በየካንቶኑ ይለያያሉ። በካንቶን Basel-Stadt ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጥዋቱ 6.00 እስከ ምሽቱ 20.00 ሰዓት ድረስ ሱቆች መክፈት ይችላሉ። የመክፈቻ ግዜውና ሰዓቱ እንደየሱቁ ይለያያል፣ ሊያጥርም ሊረዝምም ይችላል። አብዛኛዎቹ ሱቆች ቅዳሜ ከሌሎቹ ከሳምንቱ ቀናት አስቀድመው ብዙውን ግዜ በ18.00 ሰዓት ይዘጋሉ። እሁድ ግን አብዛኛዎቹ ሱቆች ዝግ ናቸው። ልዩነቱ በባቡር ጣቢያዎች፣ በነዳጅ ማደያዎች ወይም የሰፈር ውስጥ ሱቆች በተለምዶ ለ7 ቀናት ክፍት ሲሆኑ፣ ከሌሎቹም ሁሉ ቀድመው የሚከፍቱ እና ዘግይተው የሚዘጉ ናቸው።

የአስተዳደር ጽ/ቤቶች ክፍት የስራ ሰዓቶች (DE)

በህጉ መሰረት የካንቶን አስተዳድር ጽ/ቤቶች ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጥዋቱ 8.00 እስከ ቀትር 12.00 እንዲሁም ከ14.00 እስከ 17.00 ሰዓት ክፍት ናቸው። አንዳንድ ጽ/ቤቶች ከሰዓት ከኋላ ከ13.30 በኋላ ይከፍታሉ፣ ወይም በስልክ ከዚያም በላይ አገልግሎት ይሰጣሉ። አስቀድሞ በኢንተርኔት ወይም በስልክ ቢሮው መቼ ክፍት እንደሚሆን መጠየቅ ይመከራል።