የሙያ ትምህርት / መካከለኛ ትምህርት ቤት

ከግዴታ ትምህርት ቤት በኋላ አብዛኞቹ ወጣቶች የሙያ ስልጠና ይቀጥላሉ። በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለመማር ከፈለጉ፣ የሁለተኛ ደረጃ ዲፕሎማ ያስፈልግዎታል።. በመለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባካሎሬት መውሰድ ይችላሉ። በሙያ ስልጠናዎ ወቅት ባካሎሬት መውሰድ ይችላሉ።

የትምህርት አስፈላጊነት

ጥሩ ትምህርት እና ጥሩ ስራ በስዊዘርላንድ ውስጥ በጣም አስፈላጊ ናቸው። በትምህርት ቤት ጥሩ ውጤት ካገኘህ፣ በኋላ ላይ ብዙ የስራ እድሎች ይኖርሃል። ከግዴታ ትምህርት ቤት በኋላ ለሙያዊ ህይወትዎ (Sekundarstufe II). ለማዘጋጀት የተለያዩ አማራጮች አለዎት። ከተጨማሪ ስልጠና ጋር፣ ጥሩ ስራ ለማግኘት ቀላል ይሆንልዎታል።

ስለ ስልጠና እና ስለ ተጨማሪ ትምህርት ጥያቄዎች አሉዎት? የስራ፣ የጥናት እና የሙያ ምክር አገልግሎት (Berufs-, Studien- und Laufbahnberatung) ወጣቶችን እና ወላጆችን ይመክራል። የምክር አገልግሎቱ ነፃ ነው።

መሰረታዊ የሙያ ትምህርት

ከግዴታ ትምህርት በኋላ፣ አብዛኞቹ ወጣቶች መሰረታዊ የሙያ ስልጠናዎችን (የሙያ ልምምድ፣ Berufslehre). ያደርጋሉ። በሙያ ልምምድ ጊዜ በአንድ ኩባንያ ውስጥ ይሰራሉ። እዚያም ለስራዎ የሚያስፈልጉዎትን ተግባራዊ ክህሎቶች ይማራሉ።. በተጓዳኝ ወደ ሙያ ትምህርት ቤት ይሄዳሉ።. ከ250 ለሚበልጡ ሙያዎች የልምምድ ትምህርት ማድረግ ትችላለህ። ትምህርቱ በ 2 እና 4 ዓመታት መካከል ይወስዳል። በመጨረሻዎቹ ሁለት የትምህርት አመታት እራስዎ የስራ ልምድየሚያደአርጉበት ድርጅት መፈለግ አለብዎት። ትምህርት ቤቱ በዚህ ረገድ ይረዳዎታል።. ብኖም ግን ወላጆችዎም መርዳት አለባቸው። የስራ፣ የጥናት እና የሙያ የምክር አገልግሎት (Berufs-, Studien- und Laufbahnberatung) ለወጣቶች የተለያዩ አቅርቦቶች እና ምክሮች አሏቸው። የምክር አገልግሎቱ ነፃ ነው። እንዲሁም በሚለማመዱበት ወቅት ወይም በኋላ የሙያ ባካሎሬት (Berufsmaturität) ማድረግ ይችላሉ። ይህ በተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ያስችልዎታል።.

መካከለኛ ትምህርት ቤቶች

መካከለኛ ትምህርት ቤቶች (Mittelschulen) ለዩኒቨርሲቲ ወይም ለተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ (Fachhochschule) ለቀጣይ ትምህርት ያዘጋጅዎታል። ተማሪዎቹ መካከለኛ ትምህርት ቤቶች ሰፊ አጠቃላይ ትምህርት ያገኛሉ።

የተለያዩ መካከለኛ ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ፣

  • መካከለኛ ትምህርት ቤቶች ከሁለተኛ ደረጃ ባካሎሬት ጋር፡ ከዚያም በመቀጠል በዩኒቨርሲቲ መማር ይችላሉ። ነገር ግን በተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥም መማር ይችላሉ።
  • ከመካከለኛ ትምህርት ቤቶች ልዩ ባለሙያ ወይም የሙያ ባካሎሬት ያላቸው፣። ከዚያ በተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ መማር ይችላሉ። ምናልባት በዩኒቨርሲቲ ውስጥም መማር ይችላሉ።. ለዚህ ግን ፈተና ማለፍ አለብዎት። አንዳንድ ጊዜ ተጨማሪ መስፈርቶች አሉ።

አሸጋጋሪ አቅርቦቶች

ዕድሜዎ ከ18 እስከ 25 አመት ነው እና የግዴታ ትምህርትን ከጨረሱ በኋላ ወደ ባዝል-ከተማ ካንቶን አዲስ ተዛውረዋል። ምናልባትም ከማእከሉ አቅርቦቶች፣ በአሸጋጋሪ አቅርቦቶች (Brückenangebote፣ ZBA) በሚቀርበው አቅርቦት ላይ መሳተፍ ይችሉ ይሆናል። ሁሉም በስራ ህይወትዎ ውስጥ አዲስ ጥሩ ጅምር እንዲሆኖት ነው።. አሸጋጋሪ አቅርቦት ተለማማጅነት ወይም ልምምድ ለማግኘት ይረዳዎታል። ፍላጎት አለዎት? ካለዎት በአሸጋጋሪ አቅርቦቶች ማእከልን ያነጋግሩ (Zentrum für Brückenangebote)።.