ታክስ

የቀረጥ ክምችት በስዊዘርላንድ እንደምትኖርበት አካባቢ ይለያያል። ለግለሰቦች አስፈላጊ የሆኑ ታክሶች የገቢ፣ የንብረት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ናቸው።

የታክስ ስርዓት

በስዊዘርላንድ፣ በፌደራል፣ በካንቶኖች፣ በኮምዩን ደረጃ እና ሕዝባዊ በሕግ መብት ያላቸው ሃይማኖታዊ ማህበረሰቦች ታክስ (Steuern) ያስከፍላሉ። ቀጥታዊ ታክስ እና ቀጥታዊ ያልሆንኑ የታክስ ዓይነቶችን መለየት ያስፈልጋል። ቀጥታዊ ከሆኑ የታክስ ዓይነቶች መካከል በተለይም የተጨማሪ እሴት፣ የገቢ እና የንብረት ታክሶች በተጨማሪም የትምባሆ ታክስ ወይም የነዳጅ ታክሶች ናቸው። እነዚህ ታክሶች በዕቃዎቹ ዋጋ ውስጥ ተካተዋል። ታክሶችን በሚመለከት የካንቶኖችና የኮምዩኖች ሃላፊነት ስለሆነ ቀጥታዊ የሆኑ የታክስ ዓይነቶች እንደ መኖሪያው አካባቢ ከፍታኝ ልዩነት አላቸው። ባለትዳሮች በአንድ ላይ ነው ታክስ የሚከፍሉት።

ተቀናሽ ታክስ

አዲስ የመጡ የውጭ ዜጎች የገቢ ታክስ በቀጥታ ከደሞዛቸው ይቆረጣል። (ተቀናሽ ታክስ፣ Quellensteuer).ነው። ምዝገባ የሚከናወነው ለሠራተኞች በአሠሪው ነው።

  • የታክሱ መጠኑ በገቢ፣ በጋብቻ ሁኔታ (ያላገባ፣ ባለትዳር፣ የተፋታ) እና በልጆች ብዛት ላይ የተመሰረተ ነው። ለውጦች ካሉ ወዲያውኑ ሪፖርት መደረግ አለባቸው።
  • ከተቀናሽ ታክሶች በተጨማሪ የተለያዩ ሌሎች ተቀናሽ ታክሶች ለምሳሌ ለ 3 ኛ ምሰሶ 3. Säule፣ የዕዳ ወለድ፣ ከፍተኛ የህክምና ወጪዎች፣ ወዘተ
  • ንብረቶች ካሉዎት፣ ማስታወቅ እና ቀረጡን ለብቻው ለይተው መክፈል አለቦት።
  • በዓመት ከ120,000 ፍራንክ ገቢ በላይ ያለው ሰው፣ በየዓመቱ ታክስ ማወራረድ አለበት (መደበኛ ታክስ)።
  • የስዊዝ ፓስፖርት ወይም ሲ የመኖሪያ ፍቃድ ካለው የትዳር ጓደኛ ጋር ከተጋቡ በየዓመቱ ታክስ ማወራረድ (መደበኛ ግብር) አለበት።

የካንቶናል ታክስ አስተዳደር ጽ/ቤት (Kantonale Steuerverwaltung) ስለ ተቀናሽ ታክስ ተጨማሪ መረጃ ይሰጣል። የካንቶናል ታክስ አስተዳደር ጽ/ቤት ስለ ንብረቶች ቀረጥ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።

መደበኛ ግብር

የስዊዝ ፓስፖርት ወይም የ C የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ሰዎች በመደበኛነት ቀረጥ ይከፍላሉ (ordentliche Besteuerung) ።ግብሩ ከደሞዝዎ አይቀነስም። በየዓመቱ ታክስ ማወራረድ እና ግብሩን በክፍያ መጠየቂያ መክፈል አለቦት። ታክስ ማወራረድም በኦን ላይን በመስመር ላይ ሊሞሉ ይችላሉ። የቅድሚያ ክፍያ (Vorauszahlung) መክፈል ይመከራል።የሚጠበቀው የታክስ መጠን የታክስ ስሌት ማስያ (Steuerrechner) በመጠቀም ሊሰላ ይችላል።. ታክስ ማወራረጃ ቅጹን መሙላት ለስዊዘርላንድ ዜጎችም ጭምር ውስብስብጋ አዳጋች ነው። ስለዚህ በተለይ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሞሉ ታክስ ለማወራረድ የሚያግዞት ቢኖር ይመረጣል።