በሞት ጊዜ

ከቤተሰብዎ ውስጥ አንድ ሰው ከሞተ ለሚመለከተው ጽ/ቤት ሪፖርት ማድረግ አለብዎት። ከፈለጉ፣ ባለስልጣን መ/ቤቱ የቀብር ስነስርዓት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ጋር ይደውላል። የቀብር ሥነ ሥርዓት አስፈፃሚው ድርጅት አስከሬኑን ወደ መቃብር ወይም ወደ ውጭ አገር ያጓጉዛል።

ሞትን ማመልከት/ማስታወቅ

ከቤተሰብዎ ውስጥ አንድ ሰው ከሞተ፣ ሐኪም የሞት የምስክር ወረቀት ፎርም መሙላት አለበት። ከዚያ በኋላ፣ ሞቱን ለባዝል- ከተማ Basel-Stadt መዝገብ ቤት ማሳወቅ አለብዎት።

ሟቹ በሆስፒታል፣ በጡረታ ቤት ወይም በአረጋውያን መንከባከቢያ ውስጥ ቢሞት፡-

• የሆስፒታሉ ወይም የአረጋውያን መንከባከቢያው አስተዳዳሪ መሞቱን ለመዝጋቢ ጽ/ቤት ማሳወቅ አለበት።

ሰውዬው ሌላ ቦታ ከሞተ፡-

• እርሶ እንደ ዘመድ፣ ሞትን ለባዝል-ከተማ ካንቶን Basel-Stadt መዝገብ ቤት ማሳወቅ አለብዎት።

በBasel-Stadt ካንቶን ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ ነጻ ቀብር ወይም ሬሳው ከተቃጠለ አመዱ ነፃ ቀብር ያገኛል።

ወደ ውጭ አገር መመለስ/ማሰናበት

በባዝል-ከተማ ካንቶን Basel-Stadt ውስጥ ከቤተሰብዎ የሆነ ሰው ሞቶ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ግን የእርስዎ ፍላጎት ሟቹ ውጭ አገር እንዲቀበር ነው። የተፈቀደለት የቀብር ስነስርዓት ፈፃሚ ድርጅት ለዚህ ፕሮቶኮል ማሟላትት አለበት። ፕሮቶኮሉ "የሬሳ ሳጥን እና ማሸግያ ፕሮቶኮል" ይባላል። ዋናውን ፕሮቶኮል ለBasel-Stadt ካንቶን የቀብር ስነስራዓት አስፈፃሚ ማሳየት አለብዎት። ከዚያም የቀብር ስነስራዓት አስፈፃሚ ድርጅቱ የሞት የምስክር ወረቀት ይሰጣል። በእነዚህ ሰነዶች ብቻ ቀባሪው አስከሬን እንዲቀበር ወደ ውጭ ኣገር መቃብር ማጓጓዝ ይችላል። እርስዎ፣ የቤተሰብ አባል እንደመሆንዎ መጠን፣ ወጪውንን መክፈል አለብዎት።