ወላጅ መሆን

ልጅ ማሳደግ ቀላል አይደለም። አንዳንድ ጊዜ ምናልባት ለልጅዎ ምንድነው የበለጠ ጥሩ የሚሆነው ብለው ሊያስቡ ይችላሉ። ከሌሎች ወላጆች ጋር ስለ ጉዳዩ ማውራት በጣም ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። በተጨማሪም የተለያዩ የምክር አገልግሎት መስጫ ጽ/ቤቶች ሊረዱዎት ይችላሉ።

መገናኛ ማዕከላት

ለእናቶችና ለአባቶች ተብለው የተዘጋጁ ብዙ አቅርቦቶች አሉ። እዚህ ከሌሎች ወላጆች ጋር መነጋገር ወይም ከልጆችዎ ጋር በአንድ ላይ አንድ ነገር ማድረግ ይችላሉ።

  • ዳዴ የሚሉ የሕጻናት ግሩፖች (Krabbelgruppen) ለሕጻናቶች እና ዕድሜያቸው እስከ 2 ኣመት ድረስ ለሆኑ ለትንሽ ልጆች ናቸው። በዛውም ከሌሎች ወላጆች ጋር እንዲተዋውቁ ያስችሎታል።
  • የወላጆች እና የልጆች ጅምናስቲክ (MuKi-ጅምናስቲክ፣ VaKi-ጅምናስቲክ ወይም ElKi-ጅምናስቲክ) ፣ ወላጆች ከትንሽ ልጆች ጋር ነው። እርስዎም አብረው መጫወት፣ መንቀሳቀስ እና መዝናናት ይችላሉ። ብዙዎቹ ኮምዩኖች የጅምናስቲክ አቅርቦት አላቸው።
  • የመኖሪያዎ የመገናኛ ማዕከለት (Quartiertreffpunkte) ብዙ የተለያዩ ፕሮግራሞች ለወላጆችና ለልጆች አሏቸው።
  • ቤተ መጻህፍት እና ቤተ አሻንጉሊት ለትናንሾች እና ለትላልቅ ልጆች እንዲሁም ለወላጆች ብዙ አቅርቦቶች አሏቸው።

ትምህርት ለወላጆች

በBasel-Stadt በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለወላጆች የሚሰጡ ኮርሶች አሉ። ለስደተኞችም እንዲሁ የተለዩ ኮርሶች አሉ። ለምሳሌ ያህል ስለ ስዊዘርላንድ የትምህርት ስርዓት እና እንዲሁም በሌላ ቋንቋ የሚሰጡ ኮርሶችም አሉ።

ትምህርታዊ ምክር

ስለ ልጆችዎ ትምህርት ጥያቄዎች ካለዎት፣ ብዙ የተለያዩ የምክር አገልግሎት ጽ/ቤቶች ያግዝዎታል።

ለምሳሌ ያህል የሕጻናቶች እና ዕድሜያቸው እስከ 5 ዓመት የደረሱ ትናንሽ ልጆች በሚመለከት ወደ የወላጆች የምክር አገልግሎት ቢሮ (Elternberatung) ይሂዱ።

አስቸኳይ ጥያቄዎች ካሉዎት ወደ የወላጆች የአደጋ ጊዜ ስልክ ቁጥር መደወል ይችላሉ። እዛም ከባለሙያዎች የምክር አገልግሎት ያገኛሉ። በሚደውሉበት ግዜ መደበኛ የቤት ስልክ ክፍያ ነው የሚከፍሉት። ቴለፎን፣ 0848 35 45 55 ይደውሉ ወይም በኢ-ሜል ይጻፉ። አድራሻውን በ www.elternnotruf.ch. ድረ ገጽ ላይ ያገኛሉ።