የግዴታ ጋብቻ እና የሴት ልጅ ግርዛት

በስዊዘርላንድ ውስጥ የግዳጅ ጋብቻ (Zwangsheirat) እና የሴት ልጅ ግርዛት (Mädchenbeschneidung) የተከለከለ ነው። በተጓዳኝም ልዩ ስልጠና ከወሰዱ ባለሙያ ማዕከላት በተጨማሪ የተጎጂዎች ምክር ስጪ ማዕከላት ድጋፍ ይሰጣሉ።

በግዴታ ጋብቻ ማለት ምን ማለት ነው?

አንድ ሰው በቤተሰቡ ግፊት እና ከራሱ ፍላጎት ውጭ ሌላ ሰው እንዲያገባ ሲገደድ ይህም የግዴታ ጋብቻ ይባላል። ጋብቻው በህግ ቅቡልነት የሌለው እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። ሰዎች በትዳር ውስጥ በፍቃዳቸው ለመቆየት ወይም ለመለያየት የመምረጥ ነፃነት አላቸው። አንድ ሰው በትዳር ውስጥ ያለ ፍቃዱ ከኖረ የግዴታ ጋብቻ ነው ተብሎም ይጠራል።

የማስገደድ ምሳሌዎች፡- ማስፈራሪያዎች፣ ጥቁረች፣ የስነ ልቦና ጫና ወይም አካላዊ ጥቃትን ያካትታል።

በስዊዘርላንድ የግዳጅ ጋብቻ የተከለከለ ነው።

እገዛ

የብሔራዊ የስፔሻሊስት ክፍል 'zwangsheirat.ch' ለተጎጂዎች እና ለባለሙያዎች ሚስጥራዊ ምክሮችን በነጻ ይሰጣል፡ የእርዳታ መስመር በ0800 800 007 ወይም በኢሜል info@zwangsheirat.ch ይገኛል።

የልጃገረዶች ግርዛት ማለት ምን ማለት ነው? (DE)

በሴት ልጅ ግርዛት ወቅት፣ የሴትዋ የብልት አካል ይቆረጣል። የተለያዩ የአገራረዝ ዓይነቶች እና ልምዶች አሉ። የተገረዙ ልጃገረዶች እና ሴቶች ብዙውን ጊዜ በጤና እና በስነ-ልቦናዊ ችግር ይሠቃያሉ።

የሴት የብልት አካል መቁረጥ (መግረዝ) በህግ የተከለከለ ነው። ወላጆች የልጃቸውን መገረዝ ከስዊዘርላንድ ውጭ ካደራጁ ክስ ሊመሰረትባቸው ይችላል።

እገዛ

የሴት ብልት አካልን መገረዝ የሚቃወመው ኔትዎርክ /መረብ/ (Netzwerk gegen Mädchenbeschneidung) ወሳኝ ከሆኑ ቁልፍ ሰዎች ጋር መረጃ እና አውታረ መረቦችን ያቀርባል። ካሪታስ ስዊዘርላንድ የተጎዱ ቤተሰቦችን በነጻ እና በሚስጥር የምክር አገልግሎት ይሰጣል። 042 419 23 55 / beratung@maedchenbeschneidung.ch

የተጎጂዎች ምክር አገልግሎት ስጪ ማዕከላት (Opferhilfe) ድጋፍ ሊሰጡ ይችላሉ።