የቤት ውስጥ ጥቃት ምን ማለት ነው?

የቤት ውስጥ ጥቃት (Häusliche Gewalt) ማለት በቤተሰብ ወይም ከትዳር አጋር ጋር የሚያጋጥም ሁከት ወይም ብጥብጥ ነው። የቤት ውስጥ ጥቃት አካልን እና ስሜትን ይጎዳል። የቤት ውስጥ ጥቃት የተለያዩ ዓይነት ቅርጾች አሉት። በስዊዘርላንድ የቤት ውስጥ ጥቃት የተከለከለ ነው።

የቤት ውስጥ ጥቃት ምን ማለት ነው?

የቤት ውስጥ ጥቃት በቤተሰብ ወይም በአጋሮች መካከል የሚያጋጥም ሁከት ነው፡- ባለትዳር በሆኑ ሰዎች ወይም አብረው በሚኖሩ ወይም በነበሩ ሰዎች መካከል የሚጋጥም ጥቃት ነው። አብረው ቢኖሩም ባይኖሩም ጥቃቱ ልዩነት የለውም። በወላጆች እና በልጆች መካከል ወይም በወንድሞች/እህቶች መካከል የሚፈጠር ጥቃት የቤት ውስጥ ጥቃት ነው።

የቤት ውስጥ ግጭት እና ጥቃት ወደ አእምሮአዊ እና ሳይኮሶማቲክ በሽታዎች ሊያመራ ይችላል። በተለይም የህጻናት ጤናማ እና ማህበራዊ እድገት.ላይ ከባድ ተጽዕኖ ያመጣል። በተዘዋዋሪም የቤት ውስጥ ጥቃትበሚፈጸምበት ግዜ ህጻናት በተዘዋዋሪ አደጋ ላይ ስለሚወድቁ ይጎዳሉ።

ጥቃት የደረሰበት ማነው ?

ሁሉም ሰው በቤት ውስጥ ጥቃት ምክንያት ሊጎዳ ይችላል-ወጣቶች እና አዛውንቶች፣ የስዊስ ፓስፖርት ያላቸው እና የሌላቸው፣ ሀብታም እና ድሃ ቤተሰቦች በአጠቃላይ ሁሉም ሰው ። በስዊዘርላንድ ውስጥ ያሉ ብዙ ሰዎች በቤተሰባቸው ወይም (በቀድሞ) አጋራቸው በዓመፅ ምክንያት ይሰቃያሉ። ተጎጂዎች ራሳቸው እርዳታ ቢፈልጉ ጥሩ ነው።

የተለያዩ ዓይነት ቅርጾች

የተለያዩ የቤት ውስጥ የቤት ውስጥ የጥቃት ዓይነቶች አሉ። - አካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊ፣ ወሲባዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥቃቶች። ብዙውን ጊዜ የተለያዩ የጥቃት ዓይነቶች በአንድ ጊዜ ይከሰታሉ።

ለምሳሌ፡ የማያቋርጥ ስድብ፣ ግንኙነት ማድረግን መከልከል፣ ማሰር፣ መግፋት፣ መቆጣጠር፣ አንድን ሰው ወሲብ እንዲፈጽም ማስገደድ፣ ገንዘብ መንጠቅ፣ አንድን ሰው ቋንቋ እንዳይማር መከልከል እና ልጆችን ችላ ማለት ነው። ማስፈራሪያዎች ጭምር ከቤት ውስጥ ጥቃት ዓይነቶች ውስጥ ይካተታሉ።

የቤት ውስጥ ጥቃት የተከለከለ ነው

የቤት ውስጥ ጥቃት የተከለከለ ነው። በህግ ያስጠይቃል። ፖሊስ የቤት ውስጥ ጥቃት እንዳለ ካወቀ፣ ጥቃቱ የደረሰበት ሰው ባይፈልግም እንኳን ምርመራ ማድረግ አለበት ።

ከተጎጂዎች ድጋፍ ምክር አገልግሎት ማእከላት የሚሰጡ ድጋፎች (DE)

የተጎጂዎች ድጋፍ ምክር አገልግሎት ማእከላት (Opferhilfe) በቤተሰቦቻቸው ወይም በቀድሞ አጋራቸው ጥቃት የሚደርስባቸውን ሰዎች ይመክራሉ እናም መረጃም ይሰጣሉ። ይህ እርዳታ ከክፍያ ነጻ ነው። ተጎጂዎች ቀጣዩን እርምጃቸውን ከልዩ ባለሙያው ጋር አብረው ማቀድ ይችላሉ።

የድጋፍ ምክር አገልግሎት ማእከላት ሰራተኞቹ ምስጢርን ይጠብቃሉ። ይህም ማለት ስለሚደረገው ውይይት ለሌላ ሰው ማሳወቅ አይፈቀድላቸውም ማለት ነው። ለፖሊስም እንኳን ቢሆንም ለሌላ አካልት ማሳወቅ አይፈቀድለትም።