ጾታዊ/ወሲባዊ/ ጥቃት

ወሲባዊ ጥቃቶች በቀድሞ አጋሮች እና በባለትዳሮች መካከል ይከሰታሉ። ወሲባዊ ጥቃት የቤት ውስጥ የጥቃት አይነት ነው። ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ይችላል። ምንም እንኳን ተጎጂው ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ባይፈልግም፣ ከጥቃቱ በኋላ በፍጥነት የሕክምና ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ነው።

የሕክምና እርዳታ

የሴቶች ክሊኒክ ወይም የባዝል የዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የድንገተኛ ማእከል አስተማማኝ የሆኑ ሚስጥራቸው የተጠበቁ ሕክምናዎችን ያካሂዳል።

  • ሀኪሙ ስለ ምርመራው ለማንም አይናገርም።
  • ማንኛውም ጥቃት ይመዘገባል። ማስረጃዎቹ ለ1 ዓመታት ያህል ይቀመጣሉ።
  • ሰነዶቹ በኋላ ለፖሊስ ሊሰጡ ይችላሉ። ጠቃሚ ማስረጃዎች ናቸው።
  • ሀኪሙ ከተጎጂዎች ድጋፍ ስጪ የምክር ማእከላት ጋር በኔት ዎርክ ግንኙነት መፍጠር ይችላል።

አመጽ ከተፈጸመበት ጊዜ እና በምርመራው ግዜ መካከል ስላለው ሁኔታ (DE)

  • ገላቸውን እና እጃቸውን ምንም ነገር መታጠብ የለባቸውም።
  • በተቻለ መጠን ወደ መጸዳጃ ቤት መሄድ የለባቸውም።
  • ልብሳቸውን ሳያጥቡ ወደ ምርመራው ቦታ ልብሱን ይዘው መምጣት አለባቸው።

የሕግ እና የስነ-ልቦና ምክር አገልግሎት (DE)

ለተጎጂዎች የምክር አገልግሎት ስጪ ማዕከላት (Opferhilfe) የህግ እና የስነ-ልቦና ድጋፍ ሊሰጡ ይችላሉ። ለብዙ ጥያቄዎች ተገቢውን መልስ ይሰጣሉ። እዚህም ተጨማሪ ሌሎች ድጋፎችን ማግኘት ይችላሉ።

ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ

ጾታዊ ጥቃትን በሚመለከት ፖሊሶች ጥቃት ሪፖርት ሲደረግ የመቀበል እና የመመዝገብ በቂ ተሞክሮ አላቸው። ቃለ መጠይቆች የሚካሄዱት ተመሳሳይ ጾታ ባለው ሰው ነው። ቅሬታው በፖሊስ ጣቢያ ሊቀርብ ይችላል። የሚያምኑትን ሰው ወይም ከተጎጂዎች ምክር ስጪ ማዕከላት ልዩ ባለሙያ ሪፖርት ለማደረግ ይዘው መምጣት ይችላሉ።

ከስራ ሰዓታት ውጪ ፖሊስጋ በአደጋ ጊዜ ስልክ 117 ወይም 112 መደወል ይቻላል።

የካንቶኑ ፖሊስ ማህበራዊ አገልግሎት (Sozialdienst) በቤት ውስጥ እና በፆታዊ ጥቃት ላይ የተለየ ሙያዊ ዕውቀት አላቸው።

  • የካንቶኑ ፖሊስ ማህበራዊ አገልግሎት ስልክ ቁጥር 061 267 70 38 (በቢሮ የስራ ሰዓት)