በጥቂት ገንዘብ መኖር

የስዊዘርላንድ ሕይወት በአንጻራዊነት ውድ ነው። ስለዚህ ያገለገሉ አንዳንድ ዕቃዎችን መግዛት ሊጥቅም ይችላል። ገንዘብ የእጥረት ያለበት ሰው፣ በልዩ ቅናሽ ሱቆች ውስጥ በርካሽ መግዛት ይችላል።

ያገለገሉ ዕቃዎች

በስዊዘርላንድ ውስጥ ብዙ የቁጠባ መደብሮች (Brockenhäuser) አሉ። ያገለገሉ ዕቃዎች እዚያ በጣም በርካሽ መግዛት ይችላል። ነጋዴ ያልሆኑ ግለሰቦች ያገለገሉ ዕቃዎችን ለሽያጭ በልዩ ገበያዎች ያቀርባሉ። ምሳሌዎች ተንቀሳቃሽ ገበያዎች (Flohmärkte)፣ የልብስ ልውውጥ፣ የበረዶ መንሸራተቻዎች፣ ወዘተ በቅናሽ ይሸጣሉ። ኢንተርኔት ፖርታሎች ያገለገሉ ዕቃዎችን ለመግዛት እና ለመሸጥም በጣም ተወዳጅ ናቸው።

ስፖርት / ባህል / ትምህርት

በKulturlegi መታወቂያ ካርድ፣ በቂ ገንዘብ የሌላቸው ሰዎች ለመዝናኛ፣ ለስፖርት፣ ለባህላዊ እና ትምህርታዊ ዝግጅቶች ቅናሽ ያገኛሉ። ካርዱን ለማግኘት በካሪታስ ማመልከት ይቻላል። ካሪታስ መረጃ ይሰጣል እናም በመቀጠልም የKulturlegi መታወቂያ ካርድ ለማግኘት መብት እንዳለህ ያጣራል። እንደዚሁም በFamilienpass፣ በFamilienpassPlus ወይም colorkey ለብዙ ዝግጅቶች ቅናሾችን ያገኛሉ።

የካሪታስ ሱቅ

ጥቂት ገንዘብ ያላቸው ሰዎች በካሪታስ ሱቆች (Caritas Markt) ውስጥ ምግቦች እና የዕለት ተዕለት ምርቶችን በጣም በተመጣጣነ ዋጋ መግዛት ይችላሉ። ለዚህ ልዩ ካርድ ያስፈልግዎታል፣ ይህንንም ለማግኘት ካሪታስ ማመልከት አለብዎት። ካሪታስ መረጃ ይሰጥዎታል እና ካርዱን የማግኘት መብት እንዳለዎት ያጣራል። ባዝል ውስጥ አንድ የካሪታስ ሱቅ አለ።

የመንግስት ድጋፍ

ለመኖር በጣም አነስተኛ ገንዘብ ያለው ሰው፣ በብዙ መስክ የመንግስት ድጋፍ የማግኘት መብት አለው። ለምሳሌ፣ ቅናሽ የጤና ኢንሹራንስ ፕሬምየም ወይም ለሥልጠና ስኮላርሺፕ ማመልከት ይቻላል። በተወሰኑ የህይወት ሁኔታዎች ውስጥ ከማህበራዊ የድህነት ኢንሹራንስ ወይም ከማህበራዊ እርዳታ ገንዘብ ማግኘት ይቻላል። በቂ ገንዘብ የሌላቸው ቤተሰቦች በተወሰኑ ሁኔታዎች መስፈርቱን ካሟሉ የቤተሰብ የኪራይ ድጎማ (Familienmietzinsbeiträge). ማመልከት ይችላሉ።