የቤት እንስሳዎች

የቤት እንስሳ የሚያኖር ሰው፣ የተለያዩ ሕጎችን ማክበር አለበት። ለምሳሌ አንዳንድ የእንስሳት ዝርያዎች በእያንዳንዱ ቤት ውስጥ ሊቀመጡ አይችሉም። ውሻዎች የካንቶኑ ውስጥ መመዝገብ አለባቸው።

የቤት እንስሳ ማኖር

በኪራይ ቤት ውስጥ የሚኖር ሰው፣ ጥቃቅን እንስሳዎች እንደ ጊኒ አሳማ፣ ሃምስተር /ትንሽ አይጥ/፣ የካናሪያ ወፎች ወይም አሳዎች የመሳሰሉ ማኖር ይፈቀድለታል። ነገር ግን በኪራይ ውል ውስጥ ትላልቅ እንስሳትን ማኖርና ማቆየት (ድመቶችን ወይም ትናንሽ ውሻዎችን ጭምር) ክልክል ሊሆን ይችላል። እንዲሁም ጫጫታ የሚፈጥሩ እንስሳት ወይም አደገኛ የሆኑ እንስሳትን በሚመለከት የቤት አከራዩ መከልከል ይችላል። በተጨማሪም የእንስሳት ባለቤቶች የእንስሳት ጥበቃ ሕጎችን ማክበር አለባቸው። ለምሳሌ አንዳንድ እንስሳቶች ለብቻቸው መሆን የሌለባቸው እንስሳት ብቻቸውን ማኖር አይፈቀድም (ለምሳሌ ያህል ጥንቸል)።. እንዲሁም የኬጅ/የእንስሳት ጎጆ/ መጠን እና መሳሪያዎችን በሚመለክት አነስተኛ መስፈርቶች አሉ።. ብዙ እንስሳት (ብርቅዬ እንስሳት) ወደ ስዊዘርላንድ እንዲገቡ አይፈቀድም። በተረፈ ለሌሎች እንስሳት የእንስሳት ህክምና ተቋም ልዩ ፈቃድ ያስፈልጋል።

ውሻዎች

በBasel-Stadt ካንቶን ውስጥ ልዩ የውሻ ሕግ አለ። የውሻ ባለቤቶች ያለባቸውን ግዴታ በሚመለከት ሕጉ ላይ ሰፍሯል። ተጨማሪ መረጃ የእንስሳት ሃኪም ማግኘት ይቻላል።

  • በስዊዘርላንድ ውሻዎች ማይክሮ ቺፕ ሊኖራቸው ይገባል። ይህም በዳታ ባንክ መስፈር አለበት። ውሻው (የክሬዲት ካርድ ቅርጽ ያለው) የውሻ መታወቂያ ይሰጠዋል። ይህም ከትውልድ አገር መታወቂያ ጋር፣ ማለትም አንድን እንስሳ ወደ ኤውሮጳ ህብረት አገሮች ማጓጓዝ ከሚያስችለው መታወቂያ ጋር ተመሳሳይ አይደለም።
  • ውሻዎች በካንቶን መመዝገብ አለባቸው፣ ይህንን በሚመለከት ኦን ላይን ላይ የመዝገቢያ ቅጽ አለ። በየዓመቱ ግብር መከፈል አለበት። በተጨማሪም ውሻን ለማኖር ለእያንዳንዱ ውሻ የሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ (Haftpflichtversicherung) መግባት ግድ ይላል።
  • ሁሉም የውሻ ባለቤቶች የውሻቸውን ሰገራ የማንሳት እና የማስወገድ ሃላፊነት አለባቸው። ይህንን ያልፈጸመ፣ መቀጮ ይቀጣል።
  • አንዳንድ የውሻ ዘሮች ልዩ ፈቃድ ያስፈልጋቸዋል። (ለምሳሌ ፒትቡል ወይም ሮትቫይለር).
  • ውሻዎች በከተማ መናፈሻዎች እና በልጆች መጫወቻ ሜዳዎች ውስጥ በአጠቃላይ መግባት አይፈቀድም።

በካንቶኑ ካርታ "Mapserver" ላይ የውሻዎች ነጻ የመጫወቻ ዞኖች እና የውሻ መታጠቢያ ቦታዎች ምልክት ተደርጎባቸዋል።