አፓርታማ / ቤት ማግኘት

በስዊዘርላንድ የሚኖሩ አብዛኛዎቹ ሰዎች በኪራይ አፓርታማ ውስጥ ይኖራሉ። አፓርታማ ማግኘት ሁልጊዜም ቀላል አይደለም እና ኪራዩም ከፍተኛ ነው።

የመኖሪያ ቤት ገበያ

አብዛኛው የስዊስ ነዋሪዎች የሚኖሩት በኪራይ አፓርታማ ነው። የግንባታ መሬት መገንባት እጥረት ስላለ በተለይ በከተሞች እና በመሐል ከተማ ውስጥ ብዙ ነጻ የሆኑ አፓርታማዎች አይገኙም። የኪራይ ዋጋ ከፍተኛ ነው። ከገቢዎ ውስጥ አንድ አራተኛውን ለቤት ኪራይ ማውጣት ያልተለመደ ነገር አይደለም። ከመሐል ከተማ ውጭ አፓርታማ መፈለግ ያዋጣል። በቤቶች ህብረት ስራ ማህበራት ውስጥ ያለው ኪራይ አብዛኛውን ጊዜ ዝቅተኛ ነው። የቤት ኪራይ ውል ከመፈጸሙ በፊት ለዚሁ ዓላማ የኅብረት ሥራ ማህበሩ የአባልነት ድርሻ (Anteilsscheine) መጀመሪያ ላይ መግዛት አለባቸው። የገቢ መጠናቸው ትንሽ የሆኑ ቤተሰቦች እንደ ሁኔታው መስፈርቱን ካሟሉ የቤተሰብ የኪራይ የድጋፍ ድጎማ (Familienmietzinsbeiträge). ማመልከት ይችላሉ።

አፓርታማ / ቤት መፈለግ

የአፓርትማ የመኖሪያ ቤት አቅርቦቶች በብዙ የኢንተርኔት ድረ-ገጾች ላይ ይገኛል።. በክልሉ ጋዜጦች የሪል እስቴት እና የኮንዶሚዬም ማስታወቂያዎች አምድ ላይም ለህዝብ ይቀርባሉ። አንዳንድ አከራዮች በገበያ ማእከላት ወይም በሌሎች ቦታዎች አፓርታማቸውን በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ለህዝብ ያስተዋውቃሉ። ይሁን እንጂ ብዙ ነጻ አፓርታማዎች በይፋ ለህዝም አይተዋወቁም።.በዚህ ምክንያት ዘመዶችዎን ወይም የሚያውቋቸውን ሰዎች መጠየቅ እና ማዳመጥ ጥሩ አማራጭ ነው።.

የቤት ተከራይ የኪራይ ማመልከቻ

አፓርታማ ለመከራየት ፍላጎት ያለው ማንኛውም ሰው አብዛኛውን ጊዜ ባለንብረቱን ወይም የንብረት አስተዳደር ኩባንያውን ር ግንኙነት ፈጥሮ የቤት ጉብኝት ቀጠሮ ማዘጋጀት አለበት።. ለአፓርታማው ማመልከት የፈለገ ሰው አብዛኛውን ጊዜ የኪራይ የማመልከቻ ቅጽ መሙላት አለበት።. በተጨማሪም፣ አብዛኛዎቹ አከራዮች የዕዳ ማስፈጸሚያ የምዝገባ መዝገብ ኮፒ (Betreibungsregisterauszug) እና በጥቅሉ ስለ ተከራዩ የገቢ ሁኔታ መረጃ ይጠይቃሉ። ይህም የተከራዩን የመክፈል አቅሙን ለመፈተሽ ነው።. ኮፒውን ከሚመለከተው የዕዳ ማስፈጸሚያ ጽ/ቤት (Betreibungsamt). ማግኘት ይችላል።. ብዙውን ጊዜ ለአፓርትመንት ብዙ አመልካቾች ስላሉ ለተለያዩ አፓርታማዎች በተመሳሳይ ጊዜ ማመልከት ጥሩ ነው።.

አፓርታማ / ቤት መግዛት

የC የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው የውጭ አገር ሰዎች በ Basel-Stadt ካንቶን ውስጥ ያለገደብ አፓርታማዎችን ወይም ቤቶችን መግዛት ይችላሉ። ይህም ለሁሉም የB የመኖሪያ ፈቃድ ላላቸው የEU/EFTA ነዋሪዎችን ጭምር ይመለከታል። B የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ከሌሎች አገራት ለመጡ ነዋሪዎች አንድ አፓርታማ ወይም አንድ ቤት መግዛት የሚችሉት፣ ይህም ራሳቸው ውስጡ የሚኖሩ ከሆነ ብቻ ነው። የግዢ ውሉ ውስጥ ገዢው ራሱ ለመኖር ካላሰበ፣ ለግዢው ልዩ ፈቃድ ያስፈልገዋል።. በማንኛውም ሁኔታ ለሪል እስቴት እና ለኮንዶሚዬም ግዢ ኖታሪ ያስፈልጋል።. ሌሎች የመኖሪያ ፍቃዶች (L F) ያላቸው ነዋሪዎች አፓርታማዎችን ወይም ቤቶችን መግዛት አይችሉም።. የበለጠ ዝርዝር መረጃ ከኪራይ ክርክር ያስታራቂ ቦርድ (Schlichtungsstelle für Mietstreitigkeiten) ማግኘት ይቻላል።