ህመም እና አደጋ

በስዊዘርላንድ ውስጥ የሚኖር ማንኛውም ሰው የአደጋ እና የጤና መድን ሊኖረው ይገባል። እነዚህ የግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች በአደጋ፣ በህመም ወይም በእርግዝና ወቅት ወጪዎችን ይሸፍናሉ። ሁለቱም ኢንሹራንስዎች ስዊዝ በገቡ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ውስጥ የኢንሹራንስ ውሉ መፈጸም አለበት።

የጤና እንክብካቤ ኢንሹራንስ (መሰረታዊ ኢንሹራንስ)

ሁሉም የስዊዘርላንድ ነዋሪዎች የጤና መድህን (መሰረታዊ ኢንሹራንስ፣ Grundversicherung) በራሱ ተነሳሽነት ውል መፈጸም አለበት። ወደ ስዊዘርላንድ የሚሄድ ማንኛውም ሰው ይህን ለመፈጸም ሦስት ወር ጊዜ አለው። በዚህ ጊዜ ውስጥ ከታመሙ፣ ወጪዎቹ እንዲሁ ወደ ኋላ ታሳቢ ተደርገው ይሸፈናሉ። መሰረታዊ ኢንሹራንሶች ብዙ የግል የጤና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች (Krankenkassen) አቅሮት አላቸው። የጤና ኢንሹራንስ ኩባንያዎን ለመምረጥ ነፃ ነዎት። የጤና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች በስዊዘርላንድ የሚኖሩትን ሁሉ መቀበል አለባቸው።

ኢንሹራንስ የገቡ ነዋሪዎች ከገቢያቸው ወርሃዊ ክፍያ/ፕሪሚየም/ ይከፍላሉ። እነዚህ ፕሪሚየሞች እንደ ጤና ኢንሹራንስ ኩባንያ ዓይነት እና እንደ ኢንሹራንስ ሞዴላቸው ይለያያሉ። ስለዚህ ዋጋ ማወዳደር ጥቅም አለው። የጤና መድን ኢንሹራንሱን ሁል ግዜ እስከ ህዳር መጨረሻ ድረስ ለሚቀጥለው ዓመት መቀየር ይችላሉ። መሰረታዊ ኢንሹራንስ ከታመሙ ወጪዎችን ብቻ ሳይሆን ለእርግዝና እና በወሊድም ግዜ ውጪዎችን ይሸፍናል።. የሚገኙት አገልግሎቶችና ጥቅሞቹ በሕግ የተደነገጉ ናቸው።

ማሳሰቢያ፡ ለጥርስ ህክምና ወይም የመነጽር ወጪዎች አብዛኛውን ጊዜ ከራስዎ ይከፍላሉ ኣለበለዚያ ግን በፈቃደኝነት ተጨማሪ ኢንሹራንስ ከገቡ ኢንሹራንሱ ወጪውን ይሸፍናል።

የአደጋ ጊዜ ኢንሹራንስ

በሳምንት ከ8 ሰአታት በላይ ለሚሰሩ ሰራተኞች፣ በስራ ወቅት እና በነፃ በእረፍት ጊዜያቸው ለሚደርሱ አደጋዎች፣ በአሰሪው ድርጅት የአደጋ የመድን ዋስትና ተገብቶላቸዋል። ከዚህ ያነሰ ሰዓት የሚሰራ ሰው በነፃ በእረፍት ጊዜው ለሚደርሱ አደጋዎች፣ የአደጋ የመድን ዋስትና ስለሌለው፣ ራሱ በግሉ የአደጋ ኢንሹራንስ መግባት አለበት። ይህም በግል ስራ የሚተዳደሩ ሰራተኞች እና ስራ ለማይሰሩ ሰዎች፣ ከጤና ኢንሹራንስ ኩባንያቸው ጋር የአደጋ ኢንሹራንስ ውል መግባት አልባቸው። በግል ስራ የሚተዳደሩ ሰራተኞች ከሌሎች የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ጋር የአደጋ ግዜ ዋስትና ውል መፈጸም ይችላሉ። ኢንሹራንስ ገቢዎቹ ወርሃዊ ክፍያ መክፈል አለባቸው። ተቀጣሪ ሰራተኞች ክፍያው በቀጥታ ከደመወዛቸው ይቆረጣል።

የፕሪሚየም የክፍያ ቅናሽ

የጤና መድን ፕሪሚየም/ክፍያ/ መክፈል የማይችሉ ሰዎች እንደሁኔታው ለመሠረታዊ ኢንሹራንስ የፕሪሚየም የክፍያ ቅናሽ (Prämienverbilligung) ሊያገኙ ይችላሉ። ቅናሹን ለማግኘት የማመልከቻ ቅጽ ማቅረብ እና ስላለው ንብረት እና ገቢ መረጃ መሰጠት አለበት። ማመልከቻው ተቀባይነት ካገኘ፣ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ያነሰ ክፍያ ይከፈላል። የማህበራዊ ድጎማ ቢሮ ስለ የፕሪሚየም የክፍያ ቅናሽ መረጃ ይሰጣል እንዲሁም የምዝገባውን ማመልከቻ ይቀበላል።

ከመሠረታዊ ኢንሹራንስ ላይ ሌላ ተጨማሪ ኢንሹራንስ መግባት

በፈቃደኝነት ከመሠረታዊ ግዴታዊው ኢንሹራንስ ሌላ ተጨማሪ የተለያዩ ማሟያ ኢንሹራንሶች (Zusatzversicherungen) ሊገቡ ይችላሉ። እነዚህ በመሠረታዊ ኢንሹራንስ ያልተሸፈኑ አገልግሎቶች፣ ለምሳሌ እንደ የጥርስ ህክምና ያሉትን ይሸፍናሉ። ተጨማሪ ኢንሹራንሶች በሁሉም የጤና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ይሰጣል። እያንዳንዱ የጤና ኢንሹራንስ ኩባንያ ከማን ጋር ውል መፈጸም እንዳለበት እና እንድሌለበት ራሱ ይወስናል። እንዲሁም እንደ ሁኔታው ውሉ በምን ዓይነት ሁኔታ መፈጸም እንዳለበት መወሰን ይችላሉ።