ስራ አጥነት

ሁሉም ሰራተኞች የስራ አጥነት ዋስትና ኢንሹራንስ አላቸው። አብዛኛውን ጊዜ ሥራ አጥ የሆኑ ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ ያገኛሉ። ሥራ የሌላቸው ሰዎች በክልል የቅጥር ማእከል (RAV) መመዝገብ አለባቸው።. ይህም ሥራ በመፈለግ ያግዛቸዋል።

የስራ አጥነት ኢንሹራንስ

የስራ አጥነት መድን ኢንሹራንስ (ALV) የመንግስት ተቋም ሲሆን ለሁሉም ሰራተኞች ግዴታ ነው። ወርሃዊ መዋጮዎች በቀጥታ ከደመወዙ ይቀነሳሉ፣ አሠሪው ግማሹን ይከፍላል። የግል ሥራ የሚሰሩ ለሥራ አጥነት መድን ዋስትና መግባት አይችሉም። ሥራ አጥ የሆነ ማንኛውም ሰው ከሥራ አጥ ፈንድ ወርሃዊ የደመወዝ ምትክ /ድጎማ/ (Arbeitslosengeld) ይቀበላል። የሥራ አጥ ክፍያ (የሥራ አጥነት ድጎማ) መቼ እና በምን መጠን እንደሚከፈል በተለያዩ ሁኔታዎች ይወሰናል። ለምሳሌ ለምን ያህል ጊዜ እንደሰራህ ወይም ስራ አጥ የተሆነበት ምክንያቱ ይወስናል።

በስራ አጥነት ግዜ የሚወሰዱ እርምጃዎች

በመርህ ደረጃ ከመጨረሻ ከተሰራበት የሥራ ቀን በፊት በፊት፣ ቢዘገይ ሥራ አጥነት ከተሆነበት በመጀመሪያው ቀን፣ በሚመለክተው የክልሉ የቅጥር ማእከል (Regionales Arbeitsvermittlungszentrum፣ RAV) ስራ አጥነትን በሚመክት መመዝገብ ግዴታ ነው። ሁሉም ተጨማሪ ሂደቶች እዚያ ይገለጽሎታል።

ክልላዊ የስራ ቅጥር ማዕከል

ክልላዊ የስራ ቅጥር ማእከል (RAV) ሌላ ሥራ በፍጥነት እንዲያገኙ ይረዳዎታል። የሥራ አጥነት ጥቅማጥቅም የመቀበሉ ከሆነ፣ በRAV ውስጥ ያሉት የምክር ቃለ መጠይቆች ግዴታ ናቸው። በተጨማሪም RAV ኮርሶችን ወይም የቅጥር ፕሮግራሞችን ይሰጣል። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ደግሞ አስገዳጅ ናቸው። በስዊዘርላንድ ውስጥ ሰርተው የማያውቁ እና ሥራ የሚፈልጉ ሰዎች እንኳን RAV መመዝገብ ይችላሉ። ቢሆንም ግን ምንም የገንዘብ ክፍያ አያገኙም።