ማህበራዊ እርዳታ

ማህበራዊ እርዳታ ለመኖር በጣም ትንሽ ገንዘብ ላላቸው እና ከማህበራዊ ኢንሹራንስ አነስተኛ ወይም ምንም የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙ ሰዎችን ይደግፋል። ዓላማው ሰዎች በቅርብ ግዜ ውስጥ እንደገና እራሳቸውን መንከባከብ ለማስቻል ነው። ኢንሹራንስ ሳይሆን የመንግስት ድጋፍ ነው።

ማህበራዊ እርዳታ

ማህበራዊ እርዳታ (Sozialhilfe) በስዊዘርላንድ ውስጥ የተቸገሩ ሰዎችን ሁሉ ይደግፋል። አነስተኛ የኑሮ ወጪዎች ይሸፍናል። ከገንዘብ እርዳታ በተጨማሪ የምክር አገልግሎት ይሰጣል። ዓላማው ሰዎች በተቻለ በፍጥነት እንደገና በኢኮኖሚ ራሳቸውን እንዲችሉ ነው። አንድ ሰው ኑሮውን ለመደገፍ በቂ ሌላ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኝ ከሆነ፣ የማህበራዊ ዋስትና ክፍያ አይከፈለውም። ለምሳሌ ያህል፣ እንደ የሥራ አጥነት የድጎማ ገንዘብ፣ ጡረታ፣ ደመወዝ ወይም ከዘመዶች ድጋፍን ይጨምራል። ዕዳ ቢኖርም እንኳን አይከፍልም። እንደገና በቂ የፋይናንስ ምንጭ ገቢ ሲኖርዎት፣ ገንዘቡ መመለስ አለበት። ይህ ማህበራዊ እርዳታ የሚሸፈነው በግብር ከፋዮች ነው።

ለማህበራዊ እርዳታ ማመልከት

ለማህበራዊ ዕርዳታ ማመልከት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በሚኖርበት ማዘጋጃ ቤት የማህበራዊ አገልግሎት (Sozialdienst) ማመልከት አለበት። እዚያም ገቢዎን እና ንብረትዎን መግለፅ አለብዎት። ከዚያም የይገባኛል ጥያቄው ይረጋግጣል። ባለሥልጣኖቹ የድጋፉን መጠን እና ዓይነት እንደየ ሰዉ ደረጃ ይወስናሉ። ከእውነት የራቁ መልሶችን የሰጠ ወይም ዕውነታውን የደበቀ ሰው በህግ ይጠየቃል። ማህበራዊ አገልግሎቱ መመሪያዎችን ሊሰጥ እና ሁኔታዎችን መለወጥ ይችላል። መስፈርቱ ካልተሟላ፣ የሚሰጠው ማህበራዊ አገልግሎት እና ጥቅማ ጥቅሞች ሊቀነሱ ይችላሉ። በምክር ክፍለ ጊዜያት ውስጥ መሳተፍ ግዴታ ነው። ከእርሶ የሚጠበቀውን ሁሉ ማሟላት አለበዎት። ካሉበት ችግር ሁኔታውን እራስዎ ለመቀነስ የሚችሉትን ሁሉ እንዲያደርጉ ይገደዳሉ።