ቋንቋ

ለBasel-Stadt አዲስ ነዎት እና እስካሁን ድረስ ጀርመንኛ መናገር አይችሉም? በተቻሎት መጠን ቀልጥፈው ጀርመንኛ መማር አለብዎት። ቋንቋውን የሚናገሩ ከሆነ አገሪቷን እና ህዝቡን የበለጠ ማወቅ ይችላሉ። በቀላሉ ስራ እንዲያገኙ ይረዳዎታል።

መደበኛ ጀርመን ቋንቋ / የስዊዘርላንድ ጀርመንኛ (DE)

ስዊዘርላንድ አራት ብሄራዊ ቋንቋዎች አሏት፣ ጀርመንኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ጣልያንኛ እና ሮማንሽ ናቸው። የBasel-Stadt ካንቶን ኦፊሲያላዊ ቋንቋ ጀርመንኛ ነው። መደበኛ ጀርመንኛ እና የስዊዘርላንድ ጀርመንኛና ተብለው ይከፈላሉ።

  • መደበኛ የጀርመን ቋንቋ (Standarddeutsch)
    ጀርመንኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የሆኑ ስዊዘርላንዶች በመደበኛ ጀርመን ቋንቋ ነው የሚጽፉት። ት/ቤትም እና አልፎ አልፎም በራዲዮና በቴለቭዥንም ጭምር የሚናገሩት በመደበኛ ጀርመን ቋንቋ ነው፣
  • የስዊዘርላንድ ጀርመንኛና (Schweizerdeutsch)
    የስዊዘርላንድ ጀርመንኛና የጀርመን ቋንቋ ዲያሌክት ነው። ምንም እንኳን ጥሩ ጀርመንኛ መናገር ቢችሉም፣ ምናልባት የስዊዘርላንድ ጀርመንኛና ቋንቋ ለመረዳት ይከብዶት ይሆናል። ጥቂት እንኳን አይረዳዎትም? የማይረዳዎት ከሆነ ከእርሶ ጋር በመደበኛ የጀርመን ቋንቋ እንዲናገሩ መጠየቅ ይችላሉ። የግድ የስዊዘርላንድ ጀርመንኛና ቋንቋ እንዲናገሩ አይጠበቅብዎትም። ቢሆንም ግን ከተወሰነ ግዜ በኋላ ቢችሉና ቢረዳዎት መልካም ነው።

ጀርመን እና ልጆች (DE)

ልጅዎ ከጀርመን ቋንቋ ውጪ የሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ነው? ከሆነ ጀርመንኛ ቋንቋ ተናጋሪ ከሆኑ ልጆች ጋር ቀልጥፎ ቢተዋወቅ ጥሩ ነው። ይህም ልጅዎ ቋንቋ የሚማርበት ፈጣኑ መንገድ ነው። ለምሳሌ ያህል ከልጆች የጨዋታ ግሩፕ ጋር መደባለቅ አለበት። ለወላጆች እና ለልጆችም ጭምር የተመቻቸ ልዩ አቅርቦት አለ።

ልጅዎ እሰከ አሁን ድረስ ጀርመንኛ መናገር አይችልም ወይም ጥቂት ብቻ ነው የሚችለው? ይህ ከሆነ መዋዕለ ሕጻናት ከመግባቱ ቢዘገይ ከ1 ዓመት በፊት ጀርመንኛ መማር አለብት። ይህንንም በሚመለከት መዋዕለ ሕጻናት ከመጀመሩ ከ18 ወራት በፊት አስቀድመን በደብዳቤ እናስታውቆታለን። ለምሳሌ ያህል ይህ አቅርቦት የሚከተሉትን ይጨምራል፣

  • የጨዋታ ግሩፕ፣ በጀርመንኛ ድጋፍ ያለው
  • የልጆች የቀን እንክብካቤ ማዕከል (Kita)፣ ጀርመንኛ ቋንቋ የሚነገርበት
  • የቤተሰብ የቀን እንክብካቤ

እርሶም በልጅዎ የቋንቋ ዕድገት ላይ አስተዋጽዎና ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ። ከልጅዎ ጋር ብዙ ይነጋገሩ፣ ልጅዎንም ያዳምጡት እንዲሁም ታሪኮችን ይንገሩት። በሚናገሩበት ግዜም በደንብ አቀላጥፈው በሚችሉት ቋንቋ ይነጋገሩ።

የጽሑፍ ትርጉሞች / የቃል ትርጉም አገልግሎት

ለባዝል አዲስ ነዎት እና እስካሁን ድረስ ጀርመንኛ መናገር አይችሉም? ካልቻሉ አንዳንድ ግዜ እንደአስፈላጊነቱ ተርጓሚ ያስፈልጎታል። ምናልባት ዘመዶችዎን ወይም ወዳጆችዎን መጠየቅ ይችላሉ።

ይሁን እንጂ አንዳንድ ንግግሮች ለመረዳት አስቸጋሪ ወይም በጣም ግላዊ ናቸው። ለምሳሌ የሆስፒታል ወይም የአስተዳደር ጽሕፈት ቤት ቀጠሮ ሊሆን ይችላል። በባህሎች መካከል ዕውቀት ያለው ተርጓሚ ያስፈልጎት ይሆናል። እነዚህ ባለሙያዎች በተለይ ከሌላ ባህል ለመጡ ሰዎች፣ ማለትም እነዚህ ባለሙያዎች ባህልዎን ያውቃሉ እና እንዲሁም ሁሉንም መረዳት እንዲችሉ አድርገው መተርጎም ይችላሉ።

ከአስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች ደብዳቤ ተልኮሎት እና ይዘቱንም አልተረዱትም? ወይም ቅጽ መሙላት አለብዎት ወይም ደብዳቤ መጻፍ ይፈልጋሉ? ይህንን በሚመለከት እዚህ እርዳታ ያገኛሉ፣

  • GGG-Migration የትርጉም አገልግሎት ጽ/ቤት

የቋንቋ ችሎታ ደረጃዎች በውጭ ዜጎች ሕግ- እና በሲቪል ሕግ (DE)

ምናልባት „የመቆያ ፍቃድ B“ Aufenthaltsbewilligung (B) ወይም „የመኖሪያ ፈቃድ C“: Niederlassungsbewilligung (C) ማመልከት ይፈልጉ ይሆናል። ወይም ዜጋ መሆን ይፈልጉ ይሆናል። ጀርመንኛ የመጀመሪያ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎ አይደለም? ካልሆነ በቂ የጀርመንኛ ችሎታ ያሎት መሆኑን ማረጋግጫ ያስፈልጎታል።

ለማመልከትም የሚያስፈልጎትን ሙሉ መረጃዎች እዚህ ያገኛሉ፣

  • የስደተኞች አስተዳደር ጽ/ቤት (Migrationsamt)