መብት እና ግዴታ

ሰራተኞች እና አሰሪዎች የተለያዩ መብቶች እና ግዴታዎች አሏቸው። ለምሳሌ፣ ከፍተኛው የሥራ ሰዓት፣ የበዓል ቀን እና የኢንሹራንስ ሽፋን የማግኘት መብት በሕግ የተደነገገ ነው።

የስራ ውል

አብዛኛውን ግዜ በተለምዶ የቅጥር ውሎች በጽሑፍ ስምምነት መስረት ይፈጸማሉ። የቃል ኮንትራቶችም እንዲሁ ተፈጻሚት እና ተቀባይነትን ያገኛሉ። በስዊስ የግዴታ ህግ (Obligationenrecht) ህጋዊ ድንጋጌዎች መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ። አነስተኛ መሟላት ያለባቸው የሚኒሟ ደረጃዎችንም ጭምር ያካትታል።. በዚህም የተነሳ የጽሑፍ የሥራ ውል የሌላቸው ሰራኞችም ጭምር እንዲሁ የተለያዩ መብቶች እና ግዴታዎችም አላቸው።

የተቀጣሪ ሰራተኞች መብት

በስዊዘርላንድ ውስጥ ሰራተኞች የተለያዩ ህጋዊ መብቶች አሏቸው። በጣም አስፈላጊዎቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ:

  • አሰሪዎች ሰራተኞቻቸውን በማህበራዊ ኢንሹራንስ የመመዝገብ፣ የአደጋ መድን ኢንሹራንስ የማስገባት እና የተወሰነውን መዋጮ የመክፈል ግዴታ አለባቸው።
  • ሁሉም ሰራተኞች ቢያንስ ለ 4 ሳምንታት የሚከፈልበት የዕረፍት ጊዜ የማግኘት መብት አላቸው። በከፊልም በሰዓት ደመወዝ ለሚከፈላቸው ሰራተኞች ወይም የከፊል ሰዓት ለሚሠሩ ሰዎች በተመጣጣኝ ሁኔታም ይሠራል።
  • ከፍተኛ የሚፈቀደው የስራ ጊዜ በሳምንት 50 ሰዓት ነው። በአንዳንድ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ 45 ሰዓታት ብቻ ነው።.
  • ሰራተኞች በጽሁፍ የስራ ማረጋገጫ የማግኘት መብት አላቸው።
  • ማንኛውም ሰው የታመመ ወይም አደጋ ቢያጋጠመው እና በድርጅቱ ውስጥ ከሶስት ወር በላይ ከሰራ፣ ለተወሰነ ጊዜ በቀጣይነት የደመወዝ ክፍያ ይከፈለዋል።
  • ነፍሰ ጡር ሴቶች እና ልጅ የወለዱ ሴቶች ልዩ መብት አላቸው (የወሊድ ፈቃድ፣ Mutterschutz).
  • የሥርዓተ-ፆታ እኩልነት ህግ (Gleichstellungsgesetz) አንድን ሰው በሥራ ላይ በጾታ ምክንያት ማዳላትን ይከለክላል።

ደሞዝ

በBasel-Stadt ካንቶን ውስጥ በሕግ የተደነገገ አነስተኛ ደመወዝ አለ። ከጥቂቶች በስተቀር፣ ይህ በካንቶን ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ሰራተኞች ይመለከታል። በተጨማሪም፣ ብዙ ሴክተሮች ዝቅተኛ የደመወዝ ክፍያ የተደነገገው የጋራ የሥራ ስምሪት ስምምነት (Gesamtarbeitsvertrag, GAV) አላቸው።.ሴቶችና ወንዶች ለእኩል ሥራ እኩል ክፍያ የማግኘት መብት አላቸው። በሥራ ስምሪት ውል ውስጥ የተቀመጠው መጠን ጠቅላላ ደመወዝ ነው የሚሰራው። ሆኖም ግን፣ የሚከፈለው ገንዘብ የማህበራዊ ዋስትና ኢንሹራንስ መዋጮዎች ከተቀነሰ በኋላ የተጣራ ደመወዝ ነው (ማህበራዊ ተቀናሾች፣ Sozialabzüge). ለአብዛኛዎቹ የ B የመኖሪያ ፈቃድ የF ወይም N ፈቃድየአጭር ጊዜ L የመኖሪያ ፈቃድ ወይም የG ድንበር ተሻጋሪ ፈቃድ ያላቸው የተቀናሽ ግብሮች (Quellensteuer) እንዲሁም በቀጥታ ይቀነሳሉ። የግዴታ የጤና መድህን ኢንሹራንስ መጠን መዋጮ ክፍያ በስዊዘርላንድ ውስጥ የደመወዝ ተቀናሾች አካል አይደሉም።

የስራ ውል መቋረጥ

የስራ ውል መቋረጥን በሚመለከት ቀጣሪዎች እና ሰራተኞች በውሉ ውስጥ የተመለከቱትን የስራ ማብቂያ የግዜ ገደብ ማክበር አለባቸው። የጊዚ ገደቡ ሳይጠብቁና ኣስቀንመው ሳያሳውቁ በድንገት ስራ ማቋረጥ የሚፈቀው ልዩ በሆኑ ጉዳዮች ብቻ ነው። ይህ በሚከሰትበት ሁል ጊዜ የጽሁፍ ማረጋገጫ ከነ ማቋረጫ ምክንያቱ መጠየቅ ይቻላል። የታመመ፣ አደጋ የደረሰበት፣ ነብሰ ጡር የሆነ ወይም ልጅ የወለደ ማንኛውም ሰው ከስራ ያለመባረር ልዩ ጥበቃ አለው። አላግባብ ስራን ማቋረጥ/መባረር/ በሚመለከት በፍርድ ቤት መቃወም ይቻላል። ሰራተኛው እራሱ ስራ ከለቀቀ፣ ይህ ከስራ አጥነት ኢንሹራንስ የሚሰጠውን የድጋፍ መጠን ላይ ተጽዕኖ ሊያደርግ ይችላል።