የባንክ ሒሳብ/ የግብይት ክፍያዎች

ገንዘብ የሚከፈለው እና ሒሳቦች መክፈል የሚገባው ሰው የባንክ ወይም የፖስታ ቤት የባንክ ሂሳብ ያስፈልገዋል። ለግዢ ዴቢት ወይም ክሬዲት ካርዶች በብዛት ጥቅም ላይ ውለዋል በጣም ተስፋፍተዋል።

የባንክ ሒሳብ

በስዊዘርላንድ ነዋሪ የሆነ እያንዳንዱ ሰው የባንክ ሂሳብ አለው።ተቀጣሪዎች በአጠቃላይ ደመወዛቸው በባንክ ሒሳባቸው ብቻ ነው የሚከፈላቸው። በብዙ የሚቆጠሩ ባንኮች እና የፖስታ ቤት ባንኮች ለግለሰቦች የባንክ አገልግሎት ይሰጣሉ። የባንክ ሒሳብ መክፈት ብዙውን ጊዜ ነፃ ነው። ይሁን እንጂ በተለያዩ አካባቢዎች ክፍያዎች አሉ።. ጀምሮ ክፍያዎች፣ ወለዶች፣ እና የተለያዩ አገልግሎቶች አንደየ ባንኩ ክፍያ ዋጋው ይለያያል። ስለዚህ ማወዳደር ይጠቅማል። በማንኛውም አጋጣሚ ባንክ ለመክፈት ፓስፖርት ወይም ሌላ መታወቂያ ያስፈልጋል።

ዴቢት ካርድ / ክሬዲት ካርድ

የባንክ ሒሳብ ያለው ሰው ገንዘብ ለመቀበል የባንክ ካርድ ማግኘት ይኖርበታል። ይህ የሚሰራው በራሱ ባንክ ብቻ ነው። ባንኮቹ ወይም የፖስታ ባንኮቹ ግን የዴቢት ካርዶችን (ለምሳሌ Maestro) ያቀርባሉ፣ በዚህም ከሁሉም የባንክ ሂሳቦች እና ከአብዛኞቹ ሀገራት ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ እናም በብዙ የገበያ ሱቆች መጠቀም ይቻላል። እነዚህ ካርዶች በውጭ አገርም ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።. እንደ ካርዱ ዓይነት የተለያየ ዋጋ ግብር ያስከፍላል። ክሬዲት ካርዶች ለማግኘት በተለያዩ አቅራቢ ባንኮች ማመልከት ይቻላል። አገልግሎት አሰጣጡ እና የክፍያ ግብሩ ከባንክ ባንክ ይለያያል፣ ስለዚህ ማወዳደር ይጠቅማል። በዴቢት ወይም ክሬዲት ካርድ ክፍያ መፈጸም በሁሉም ቦታ ተስፋፍቷል።

ሂሳቦችን መክፈል

ብዙውን ጊዜ የሒሳብ ክፍያዎች (Rechnungen) በፖስታ ወይም በኢሜይል በመክፍያ ደረሰኝ ዝርዝር ይላካሉ። ሊታሰብባቸው የሚገቡ ሦስት የአከፋፈል አማራጮች አሉ፡-

  • ኢ-ባንኪንግ፡ በኢንተርኔት በኩል የሚደረጉ ግብይቶችን ክፍያዎች በጣም የተስፋፋ እና አስተማማኝ ናቸው።
  • በባንክ መክፍያ መስኮት፡ በመክፍያ ደረሰኝ በፖስታ ቤት በጥሬ ገንዘብ ክፍያ መክፈል ይቻላል። የፖስታ ባንክ ያለው ሰው ገንዘቡን በቀጥታ ከባንክ ሒሳቡ መክፈልና ማስተላለፍ ይቻላል። የባንክ ደንበኞች ከባንክ ክፍያዎችን በባንክ መክፍያ መስኮት ክፍያውን መፈጸም ይችላሉ።
  • በፖስታ፡- ገንዘብን ለማስተላለፍ በፖስታ አድርጎ ለባንክ ወይም ለፖስታ ቤት መላክ ይቻላል። እባክዎ ተጨማሪ መረጃው ለማግኘት ባንክ ቤት ወይም የፖስታ ቤት ባንክ ቤት ይጠይቁ።

ለሚደጋገሙ ሒሳቦች የአከፋፈል አማራጮች፡-

  • የቀጥታ ክፍያ ሂደት Load Ledger Vendor (LSV) አላላክ ምቾት ይሰጣል።ምክንያቱም የሒሳብ ክፍያው ወድያውኑ በፍጥነት ከባንክ ሒሳብ ላይ ይወስዳል። ስለ ሁኔታው ተጨማሪ መረጃው ለማግኘት ባንክ ቤት ወይም የፖስታ ባንክ ቤት ይጠይቁ።
  • ሂሳቡ ከፍ ያለ ከሆነ (ለምሳሌ ያህል የኪራይ ክፍያ) በባንክ ወይም በፖስታ ባንክ ቤት ገንዘቡ በግዜው ባንኩ እንዲያስተላልፍ ዘለቄታው ውል (Dauerauftrag) መፈጸም ይቻላል።

ክፍያዎች ሁልግዜ የክፍያ የጊዜ ገደብ አላቸው።መጠየቅ ይችላሉ። ይህ የክፍያ የጊዜ ገደብ ክፍያው ሳይፈጸም ገደቡ ቢያልፍ፣ ጣጣ ሊያመጣ ይችላል። ገንዘቡን የግድ ከነቅጣቱ ማስከፈል (Betreibung) ይቻላል።