የአረጋውያን እንክብካቤ

ለአረጋውያን የጡረታ አቅርቦት ፈንድ፣ ጡረተኞች ለመኖር የሚያስችል በቂ ገንዘብ እንዳላቸው ያረጋግጣል። የስዊዘርላንድ የጡረታ ስርዓት ሶስት ምሰሶዎች አሉት፣ የአረጋውያን እና የመበለት የመድን ኢንሹራንስ (AHV)፣ የሙያ ጡረታ (የጡረታ ፈንድ) እና በፈቃደኝነት ለአረጋውያን የጡረታ አቅርቦት ፈንድ (3ኛ ምሰሶ)።

የአረጋውያን እና የመበለቶች የመድን ኢንሹራንስ (1 ኛ ምሰሶ፣ 1. Säule)

የአረጋውያን እና የመበለቶች የመድን ኢንሹራንስ (AHV) የመንግስት ተቋም ነው። አብዛኛው አዋቂዎች ከዚህ ለመጠቀም መዋጮ መክፈል አለባቸው። መዋጮዎቹ በቀጥታ ከሠራተኞች ከወርሃዊ ደመወዛቸው ይቀነሳል። አሠሪው ግማሹን ይከፍላል። በግል ሥራ የሚተዳደሩ ሰዎች ወይም ሥራ የሌላቸው ሰዎች መዋጮውን እንዴት መክፈል እንዳለባቸው ከካሳ ቢሮ (Ausgleichskasse) መጠየቅ አለባቸው። AHV ለጡረተኞች ወርሃዊ ጡረታ ይከፍላል። የጡረታ መጠኑ እስካሁን በተከፈለው መዋጮ ብዛት ላይ የተመሰረተ ነው። ሆኖም ግን፣ AHV በተጨማሪም የሟቹን የትዳር ጓደኛ እና ልጆች በሞት ጊዜ (የመበለት እና ወላጅ አልባ ጡረታ) ይደግፋል። ሁሉም ሰው የግል የኢንሹራንስ ልዩ ቁጥሩን የያዘ የAHV ካርድ ይቀበላል።

የስራ ጡረታ (2 ኛ ምሰሶ፣ 2. Säule) (DE)

ከጡረታ በኋላ የተለመደውን ህይወትዎን ለመቀጠል አብዛኛውን ግዜ AHV ብቻውን በቂ አይደለም። ለዚያም ነው ለሠራተኞች የሥራ ጡረታ ፈንድ (የጡረታ ፈንድ፣ Pensionskasse) ያለው፣ ከተወሰነ ዓመታዊ ደመወዝ በላይ ግዴታ ነው። ለዚህ መዋጮ በቀጥታ ከወርሃዊ ደመወዝ ይቀነሳል፣ አሠሪው ቢያንስ ግማሽ መክፈል አለበት። በግል ስራ የሚተዳደሩ ምንም አይነት መዋጮ መክፈል የለባቸውም። ነገር ግን ይህንን በፈቃደኝነት ማድረግ ይችላሉ፣ የራሳቸው የግል ውሳኔ ነው። በጡረታ ፈንድ ውስጥ የተቀመጠው ገንዘብ በእርጅና ጊዜ እንደ ጡረታ ወይም እንደ አንድ ጊዜ ክፍያ ይከፈላል። በአንዳንድ የተለዩ ሁኔታዎች ሲያጋጥም ገንዘቡ ቀደም ብሎ ሊከፈል ይችላል፣-ለምሳሌ የግል ኩባንያ ለማቋቋም፣ ከስዊዘርላንድ ርቀው ሲኖሩ፣ የግል መኖሪያ ቤት ለመገንባት ወይም አፓርታማ ለመግዛት።

በፈቃደኝነት ለአረጋውያን የጡረታ አቅርቦት ፈንድ (3 ኛ ምሰሶ፣ 3. Säule) (DE)

3ኛው ምሰሶ በፈቃደኝነት ለአረጋውያን የጡረታ አቅርቦት ፈንድ ሲሆን፣ ከግብር ቅነሳን ያስገኛል። ከባንክ ወይም ከኢንሹራንስ ኩባንያዎች ጋር የስምምነቱን ውል መፈጸም ይቻላል። በእርጅና ጊዜ መጠባበቂያ እንዲኖርዎት በ3 ኛው ምሰሶ ፈንድ ገንዘብ መቆጠብ ያስችላል።

ተጨማሪ አገልግሎቶች

ምንም እንኳን አረጋውያን AHV እና የጡረታ ፈንድ ቢኖራቸውም፣ ለመኖር የሚያስችል በቂ ገንዘብ የሌላቸው አረጋውያን፣ ተጨማሪ የገንዘብ ጥቅማ ጥቅሞች (Ergänzungsleistungen). ሊያገኙ ይችላሉ። ተጨማሪ ጥቅማ ጥቅሞችን ለማግኘት ማህበራዊ ድጎማ ቢሮ ማመልከት አለባቸው። የማግኘት መብት ያለው ማን እንደሆነ በግልፅ ተቀምጧል። ተጨማሪ ጥቅማ ጥቅሞች የሚሸፈነው በግብር ከፋዮች ነው።