ጉርብትና / የሰፈር

በጎረቤቶች መካከል ያለው ግንኙነት በእያንዳንዱ ቤት ወይም ወረዳ ውስጥ እኩል አይደለም።. በማንኛውም ሁኔታ በተለይም ግጭቶች በሚፈጸሙበት ጊዜ ከጎረቤቶችዎ ጋር መነጋገር ተገቢ ነው።

ግንኙነት ማድረግ/ ጉርብትና

በአንዳንድ መኖሪያ ህንጻዎች ወይም በመኖሪያ አካባቢዎች ጎረቤቶች እርስ በርስ ይገናኛሉ (በዓል በማክበር፣ ወዘተ.). በሌሎች ቦታዎች ይህ ብዙም የተለመደ አይደለም። አዲስ ቤት የገባ ማንኛውም ሰው በእርግጠኝነት እራሱን ማስተዋወቅ ይችላል፣ ይህም በባዝል-ከተማ ካንቶን Basel-Stadt ውስጥ በጣም የተለመደ ነው። ጎረቤቶች ግኙነቱን ካልፈለጉ፣ ይህ የአዲሶቹ ተከራዮች ጥፋት መሆን የለበትም።. ከዚያ በተረፈ በቀላሉ ወዳጃዊ በሆነ መንገድ ጥሩ ጉርብትና ላይ ማተኮር ይሻላል። ከአካባቢው ህዝብ ጋር ለመገናኘት ሌሎች መንገዶችም አሉ ለምሳሌ በማህበሮች ውስጥ መሳተፍ።

የመኖሪያ ስርዓት/ደምብ

ብዙ ተከራዮች ወይም ባለቤቶች የሚኖሩበት በጋራ አንድ ህንጻ ውስጥ የቤት ውስጥ ህጎች (Hausordnung). አሉት። ይህም ህግ ብዙውን ጊዜ ከኪራይ ስምምነት ጋር አብሮ ይሰጣል። አብሮ ስለ መኖር እና እንደ የልብስ ማጠቢያ ክፍል ያሉ የጋራ ቦታዎችን ለመጠቀም ህጉ ይደነግል። በስዊዘርላንድ ውስጥ የቤት ውስጥ ደንቦች መከበር በጣም ትልቅ ዋጋ ይሰጠዋል። ይህ ከሁሉም በላይ የእረፍት የጸጥታ ጊዜዎችን ይመለከታል፣ አንዳንዶቹም እንደውም በሕግ የተደነገጉ ናቸው።.

ግጭት

በቤቱ ውስጥ ያሉ ሌሎች ሰዎች የቤቱን ህግ ካላከበሩ እና በዚህም የተነሳ አንድ ሰው የመረበሽ ስሜት ከተሰማው፣ በመጀመሪያ ከሚመለከተው ሰው ጋር ውይይት ማድረግ ይመከራል። ይህም ውጤት ካላመጣ ባለንብረቱን ወይም የንብረት አስተዳደሩን ሃላፊ ማነጋገር ይችላሉ። በከባድ ጉዳዮች፣ ለፖሊስ (ስልክ 117) ማሳወቅም ይችላሉ። በሌላ ቤት ውስጥ ጥቃትን ከተመለከቱ እና ስለ ጎረቤቶችዎ ደህንነት የሚጨነቁ ከሆነ ፖሊስ ሁል ጊዜ መጠራት አለበት።