ለጥቃት ፈጻሚዎች እርዳታ

በአካል ወይም በስሜታዊነት የተጎዳ ማንኛውም ሰው ራሱ ሀላፊነቱን መውሰድ እና እርዳታ ማግኘት አለበት። በምክር ውይይት ጊዜ አዲስ የባህሪ ለውጥ መማር ይቻላል።

እርዳታ የት ማግኘት እችላለሁ?

የቤት ውስጥ ጥቃትን በሚመለከት የሚሰጠው የትምህርት ፕሮግራም ግጭቶችን ያለ ጥቃት እንዴት መፍታት እንደሚችሉ ያስተምራል። የሚሰጠው አገልግሎት አዋቂዎችን ማእከላዊ ያደረገ ነው። የትርጉም አገልግሎትም ይኖራል። በ061 267 44 90 ወይም haeusliche-macht@jsd.bs.ch ላይ መመዝገብ ይቻላል። በነፃ ሳይከፍሉ መሳተፍ ይቻላል።

ተጨማሪ አገልግሎቶች፡-

  • የቤት ውስጥ ጥቃት በሚመለከት ስለ ግጭት የምክር አገልግሎት፣ 061 267 00 26፣ www.bdm.bs.ch (DE)
  • በባዝል ክልል የወንዶች ቢሮ፣ 061 691 02 02፣ www.mbrb.ch (DE).

የምክር ዋጋ የሚወሰነው ምክር የሚፈልገው ሰው የፋይናንስ አቅሙን ግምት ውስጥ በማስገባት ነው። በፍጥነት የልብን መነጋገር ለሚፈልግ ሰው በተዘረጉ የእርዳታ እጆች (Dargebotene Hand) (በስልክ፣ በጽሑፍ መልእክት፣ በቻት፣ በደብዳቤ) እርዳታ ማግኘት ይችላል። በማናቸውም ሰዓት መስመር ላይ የዕለቱ ተረኛ እንዲሁም ምሽት ላይ ይጠብቆታል።.ስምዎንና ማንነቶን ሳይገልጹ ስለ ችግሩ ማነጋገር ይችላሉ።

  • ለእርዳታ የተዘረጉ እጆች የእርዳታ አገልግሎት (24/7) ፣ በስልክ ቁጥር 143፣ www.143.ch ይገኛል።