በድብቅ ማሳደድ

በድብቅ ማሳደድ የጥቃት ዓይነት ሲሆን በጣም አስጨናቂም ነው። ስለጉዳዩ ማውራት እና ምክር ማግኘት አስፈላጊ ነው።

በድብቅ ማሳደድ ምንድን ነው?

በድብቅ ማሳደድ ከልክ በላይ አፍጥጦ መመልከት፣ መገናኘት፣ ክትትል ማድረግ እና ሰውን ማስጨነቅ ማለት ነው። ይህ የሚደረገው ከሚሳደደው ሰው ፍላጎት ውጭ በድብቅ ነው። አብዛኛውን ግዜ ይህን የሚያደርጉ ጥቃት ፈጻሚዎች የተጠቂው (የቀድሞ አጋሮች) የቅርብ ሰዎች ወይም እንግዳ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ።

ለምሳሌ፡- ብዙ ቁጥር ያላቸውን የጽሑፍ መልእክቶችን፣ ኢሜይሎች እና ሌሎች መልዕክቶችን መላክ፣ በሥራ ቦታ ወይም በቤት ውስጥ አድፍጦ መሰለል፣ በስልክ ሽብር መፍጠር፣ ያልተፈለጉ ስጦታዎችን መስጠት እና ስለ ግለ ሰቡ ከሚያውቁ ሰዎች አካባቢ መረጃ መፈለግ።

ተደብቆ ማሳደድ በተጎጂው ጤና ላይ አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል።

ጥቃትን መዝግቦ መያዝ

በድብቅ የማሳደድ ተግባሩን በሚመለከት ማረጋገጫ መያዝ አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ፣ የጥቃቱ ሰለባ የሆነው ግለሰብ ስለ እያንዳንዱን የማሳደድ ድርጊቶች በሚመለከት ማስታወሻ መያዝ (ለምሳሌ ስጦታዎች፣ ማስታወሻዎች፣ የስልክ ጥሪዎች)፣ ተጎጂዎች በአካባቢያቸው ላሉ ሰዎች (ጎረቤቶች፣ ጓደኞች ወይም አሰሪ) ማሳወቅ እና የማንኛውም መልእክት ቅጽበታዊ ገጽ እይታዎችን/ፎቶዎችን ማንሳት ይችላሉ (ኋትስ-አፕ፣ ፌስ-ቡክ ወዘተ)።

እርዳታ ፍለጋ

የተጎጂዎች ምክር አገልግሎት ስጪ ማዕከላት (Opferhilfe) ድጋፍ መስጠት ይችላሉ። ስፔሻሊስቶች ስለ ህግ ሁኔታው ማብራሪያ መስጠት እና ተጎጂውን በቀጣይ እርምጃዎች መደገፍ ይችላሉ።

የካንቶኑ ፖሊስ ማህበራዊ አገልግሎት ዘርፍ (Sozialdienst) ተደብቆ በማሳደድ ጥቃትን በሚመለከት ላይ ልዩ የሆነ ዕውቀት አላቸው። የጥቃት ሰለባው የሆኑ ሰዎች ከማህበራዊ አገልግሎት ዘርፉ ጋር ግንኙነት ማድረግ ይችላሉ።