ነጻ የእረፍት ግዜ

በBasel-Stadt ውስጥ ብዙ ማራኪ የሆኑ የእረፍት ግዜ ማሳለፊያና የመዝናኛ አቅርቦቶች አሉ። እነዚህም ቦታዎች አዲስ ሰው ለመተዋወቅ እና በጋራ አንድ ላይ ጊዜ ለማሳለፍ ያስችሎታል።

ማህበራት

አብዛኛዎቹ የባዝል ከተማ ነዋሪዎች የማህበራት (Verein) አባላቶች ናቸው። የተለያየ ፍላጎት ላላቸው ሰዎች እንደፍላጎታቸው ዓይነት የስፖርት ክለቦች ወይም የባህል ክለቦችና ማህበራት አሉ። ክለቦችን ወይም ማህበራትን ከተቀላቀልክ፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር እንድትተዋውቅ ይረዳሃል። አብዛኛዎቹ ማህበራት ለሁሉም ሰው ክፍት ናቸው።

አቅርቦቶች ለወጣቶች

ወጣቶች በትርፍ ጊዚያቸው ያሉትን አቅርቦቶች ቢጠቀሙ፣ ከሌሎች ከእድሜያቸው ጋር ተመጣጣኝ ከሆኑ ወጣቶች ጋር እንዲተዋወቁ ያስችላቸዋል። ፕሮጀክት ላይ መሳተፍና የራሳቸውን የግላቸውን ሃሳብ ማቅረብ ይችላሉ። ባለሙያዎች ወጣቶችን የሙያ ድጋፍ እንዲሁም አብረዋቸው በመሆን ሙያዊ ክትትል ያደርጉላቸዋል (Jugendarbeit)። በመሰረቱ አቅርቦቶቹ ከክፍያ ነጻ ናቸው።

ሽርሽር እና ባህል

በBasel-Stadt ካንቶን ውስጥ ብዙ ጉዞዎችንና ሽርሽሮችን ማድረግና የባህል ዝግጅቶችን መጎብኘት ይቻላሉ። ብዙ ሰዎች በበጋ ወቅት በራይን ወንዝ ውስጥ ይዋኛሉ ወይም በፓርክ ውስጥ ሽርሽር ያደርጋሉ። ብዙዎች ከቤተሰቦቻው ጋር ወደ ባዝል የእንስሳት ፓርክ መሄድን ይወዳሉ። በአካባቢው የሚያምሩ የእግር ጉዞ እና የብስክሌት መንገዶች አሉ። እንደ ፍራይቡርግ፣ ብራይስጋው ወይም ስትራስቡርግ ያሉ ከተሞች በባቡር በፍጥነት መድረስ ይቻላል። በBasel Tourismus የትኞቹን የሽርሽር ጉዞዎች መሄድ እንደሚችሉ እና በየትኞቹ ዝግጅቶች ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

የአካባቢ የመገናኛ ማዕከላት (DE)

የአካባቢ የመገናኛ ማዕከላት (Quartiertreffpunkte) ለሁሉም ሰው ክፍት ናቸው። ለቤተሰቦች፣ ለአረጋውያን እና ትንሽ ጀርመንኛ ለሚናገሩ ሰዎች ጭምር የሚሆኑ አቅርቦቶች አላቸው። አንዳንድ የመገናኛ መዝናኛ ማዕከላት የቤተሰብ ማዕከሎች ናቸው። የአካባቢ የመገናኛ ማዕከላት የዕለት ተዕለት ሕይወትን በሚመለከት ምክርና ድጋፍ ይሰጣሉ። በመገናኛ መዝናኛ ማዕከላት ቤተሰባዊ በዓሎችን እና ሌላ ልዩ ዝግጅቶች ለማክበር ክፍሎችን መከራየት ይቻላል።

የበጎ ፍቃድ ስራ

በበጎ ፈቃደኝነት ስራ (Freiwilligenarbeit) በአካባቢዎ /በዙርያዎ/ ያሉትን ሰዎች እና አካባቢዎን መርዳት ይችላሉ። "በጎ ፍቃድ " ማለት፣ ለስራዎ ምንም ዓይነት ደሞዝ አይቀበሉም ማለት ነው። በጎ ፈቃደኞች በስዊዘርላንድ ውስጥ በተለይም በማህበራት ውስጥ ብዙ ተግባራትን ያከናውናሉ። የበጎ ፈቃደኝነት ስራ ለመስራት ፍላጎት አለዎት? በማህበሮች በበርካታ ጉዳዮች ውስጥ ለምሳሌ ለመጥቀስ ያህል በባህል፣ በስፖርት፣ በማህበራዊ ጉዳዮች፣ በትምህርት፣ በእንስሳት ደህንነት፣ በአካባቢ በተፈጥሮ ጥበቃ ወይም በጤና ላይ መሰማራት ይችላሉ።

በበጎ ፈቃደኝነት ስራ ላይ ለመሳተፍና ለመሰማራት መረጃ እዚህ ማግኘት ይችላሉ:

  • የበጎ ፍቃድ ሥራ ኤክስፐርት ቢሮ GGG Benevol
  • የስዊዘርላንድ ቀይ መስቀል በBasel-Stadt (SRK)
  • የባዝል ከተማ ካሪታስ

በጥገኝነት ጠያቂዎች እና በስደተኞች መስክ ለመሰማራት አስፈላጊ መረጃ፡-

  • በጥገኝነት ጠያቂዎች መስክ የበጎ ፍቃድ ሥራ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (KOFF)
  • የስዊዘርላንድ የስደተኞች እርዳታ

በስፖርት፣ በባህል እና በትምህርት ዝግጅቶች ላይ ቅናሾች

"KulturLegi" የሚል መታወቂያ የሚያገለግለው ገቢያቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ሰዎች ነው። KulturLegi ካለዎት ለስፖርት፣ ባህል እና ለትምህርት ዝግጅቶች የሚከፍሉት ክፍያ አነስተኛ ነው። KulturLegi ለማግኘት ካሪታስ ማመልከት ይችላሉ። ካሪታስ ስለ KulturLegi ስለሁኔታው መረጃ ይሰጥዎታል፣ በተጨማሪም የሚገባዎት መሆኑንና አለመሆኑን ያረጋግጣል። እንዲሁም የቤተሰብ ካርድ (Familienpass) እና FamilienpassPlus ካርድ ይሰጣል። እነዚህ ካርዶች የሚያገለግሉት በሰሜናዊ ምዕራብ ስዊዘርላንድ ለሚኖሩ ነዋሪዎች ነው። ለልጆች፣ ለወጣቶች እና ለጎልማሳ ወጣቶች ብዙ ተጨማሪ ቅናሾች እና ያለ ክፍያ ነጻ አቅርቦቶች አሉ፣ ለምሳሌ "colourkey" ወይም የእረፍት ካርድ (Ferienpass). በKulturLegi የቤተሰብ ካርድ ወይም በcolorkey ብዙ አቅርቦቶች ቅናሽ ናቸው። ስለዚህ ጉዳይ በሚመለከት በበይነ መረብ በኢንተርኔት ላይ የበለጠ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።