ሃይማኖት

ስዊዘርላንድ በተለምዶ የክርስቲያን ሀገር ነች። በአሁኑ ግዜ ግን የሌላ ሃይማኖት ተከታዮች የሆኑ ብዙ ሰዎች እዚህ ይኖራሉ። በስዊዘርላንድ የሃይማኖት ነፃነት አለ፣ እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ከሃይማኖት ገለልተኛ ናቸው።

ሃይማኖትና መንግስት (DE)

ስዊዘርላንድ በተለምዶ በክርስቲያን ሃይማኖት የተቀረጸች ሃገር ናት። ካንቶኖቹ በሃይማኖትና በመንግስት መካከል ያለውን ዝምድና ይወስናሉ። እንደ አብዛኞቹ ጀርመንኛ ተናጋሪ የስዊስ ካንቶኖች ሁሉ የBasel-Stadt ካንቶን ለአንዳንድ የሃይማኖት ማህበራት ልክ እንደ የህዝብ ተቋማት እውቅና ይሰጣሉ። ይህም ማለት መንግስት ለእነሱ የተወሰኑ መብቶችን ያስተላልፋል ማለት ነው። ለምሳሌ አባሎቻቸውን ታክስ ማስከፈል ይችላሉ። የሚከተሉት የሃይማኖት ማህበራት በBasel-Stadt ካንቶን በግልጽ የሕግ ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል: የኢቫንጀሊካል ተሐድሶ ቤተ ክርስቲያን፣ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን፣ የክርስቶስ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና የአይሁድ ማኅበረሰብ፣ ሌሎች አንዳንድ ተጨማሪ ማህበራትም በካንቶን ተቀባይነትን ያገኙ አሉ። እነዚህ ማህበራት በግል በሕግ የተደራጁ ናቸው።

ሃይማኖታዊ ማህበረሰቦች በBasel-Stadt

አንድ ሶስተኛ የሚሆኑት የባዝል ነዋሪዎች ከአራቱ በህግ ዕውቅና ከተሰጣቸው ማህበረተሰቦች ያንዱ አባል ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ሌላ ብዙ ሃይማኖታዊ ማህበረተሰቦች ይገኛሉ። ለምሳሌ ያክል የእስላም፣ የሂንዱ፣ የቡዲስት ወይም አዳዲስ እንቅስቃሴዎች ፣ ከነዋሪዎቹ ግማሽ ያህሉ የአንዳቸውም የሃይማኖት ማህበረሰብ አባል አይደሉም።

የሃይማኖት ነጻነት

የስዊዘርላንድ ሕገ መንግስት የሃይማኖትን ነጻነት ያረጋግጣል። ያህም ማለት ማንኛውም ሰው ምን ዓይነት ሃይማኖትና እምነት ማመን እንዳለበት ራሱ የመወሰን መብቱ የተጠበቀ ነው። ሁሉም ሰው እምነቱን እንዲገልጽ እና እንዲያስፋፋ ተፈቅዶለታል። ማንም ሰው ማንንም ሰው ያለ ፍቃዱ ሃይማኖታዊ ማህበረሰብ ውስጥ እንዲቀላቀል ወይም በሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ እንዲካፈል ማስገደድ አይችልም። ሰዎች ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችን እና በዓላትን ለማክበር እንዲሰበሰቡ ይፈቀድላቸዋል። ሰዎች በሃይማኖታቸው ወይም በእምነታቸው ምክንያት መገለል የለባቸውም።

ሃይማኖት እና ትምህርት

ግዴታዊ ትምህርቶች ከሃይማኖት ገለልተኛ ናቸው። ይሁን እንጂ ሃይማኖታዊ ርዕሰ ጉዳዮች በክፍል ውስጥ ቦታ አላቸው። አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት «ስለ ተፈጥሮ፣ ስነ ስብ፣ ስለ ማህበረሰብ » ትምህርት ይሰጣል። እነዚህ ትምህርቶች የሚያስተምሩት ስለተለያዩ የአኗኗር ዘይቤዎች እና ባህሎች ነው። በተጓዳኝም ልጆቹ በፈቃደኝነት ሊሳተፉ የሚችሉበት የሃይማኖትና የእምነት ትምህርቶች ይሰጣሉ። በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት «ስለ ስነ ምግባር ፣ ስለ ሃይማኖትና ስለ ማህበረሰብ» ትምህርት ይሰጣል። እነዚህ ግዴታዊ ትምህርቶች ናቸው። እዚህ ተማሪዎቹ ከተለያዩ ባህሎች፣ ሃይማኖቶች፣ የዓለም አቀፋዊ እይታዎች እና ማህበራዊ እሴቶች ጋር ለመኖር የሚያስፈልጋቸውን ጠቃሚ ክህለቶችን ይማራሉ። ከሌላ እምነት ተቋም ለመጡ ተማሪዎች ሃይማኖታዊ ማህበረሰቦች ከትምህርት ቤት ውጪ አንዳንድ ጊዜ የማስተማር እድሎችን ይሰጣሉ።