ቴለቪዥን / ኢንተርኔት / ቴለፎን

ለኢንተርኔት፣ የስልክ እና የኬብል ቴሌቪዥን የተለያዩ አቅራቢዎች አሉ። አቅርቦቶቹ በከፊል ከቦታ ቦታ ይለያያሉ። ምናልባት ሁሉም ነዋሪዎች ለሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ግብር ክፍያ መክፈል አለባቸው።

የራዲዮ እና የቴለቭዥን ግብር አከፋፈል

በመሠረቱ፣ በስዊዘርላንድ ውስጥ ያሉ ሁሉም ቤቶች የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ክፍያዎችን (Radio- und Fernsehgebühren) መክፈል አለባቸው፣ የንብረቱ ዓይነት ክፍያውን አይወስነውም። በዚህ ህጋዊ የግብር ክፍያ መንግስታዊ የስዊስ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን (SRG SSR) እንዲሁም የግል ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ፕሮግራሞች ይደገፋሉ። ክፍያውን የመሰብሰብ ሃላፊነት ያለው ሴራፌ ኩባንያ ነው። የግብሩ ክፍያው በየዓመቱ ይከፈላል።. ተጨማሪ የድጋፍ ድጎማ አገልግሎቶችን የሚያገኙ ሰዎች ከክፍያ ነፃ ሊሆኑ ይችላሉ።

ቴለፎን፣ ኢንተርኔት፣ የኬብል-ቴሌቭዥን

በስዊዘርላንድ ውስጥ ለስልክ፣ ለኢንተርኔት እና ለኬብል ቴሌቪዥን የተለያዩ አቅራቢዎች አሉ። አንዳንዶቹ አገልግሎት የሚሰጡት በተወሰኑ ክልሎች ብቻ ነው። ምን ዓይነት አቅርቦት መጠቀም እንደሚቻል የሚወስነው የመኖሪያው ቦታ እና አንዳንዴም የቤቱ ዕይነት ነው። ማወዳደር ተገቢ ነው ምክንያቱም አገልግሎቶቹ እና ዋጋዎች የተለያዩ ስለሆኑ። እቤት ውስጥ የኢንተርኔት ግንኙነቶች ብዙውን ጊዜ በጣም ፈጣን ናቸው። በጣም ጥቂት ኢንተርኔት ካፌዎች ነው ያሉት፣ ምክንያቱም ሁሉም ቤቶች ማለት ይቻላል የኢንተርኔት ግንኙነት ስላላቸው።