የምክር አገልግሎት ማዕከላት

በባዝል ከተማ ካንቶን ውስጥ የተለያዩ የምክር አገልግሎት ማዕከላት አሉ። አንዳንድ ማዕከላት አጠቃላይ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ምክር ይሰጣሉ። አንዳንድ ቢሮዎች ደግሞ ለተወሰኑ ጥያቄዎች ብቻ ምክር ይሰጣሉ። የመጀመሪያው የምክር አገልግሎት ብዙውን ጊዜ ከክፍያ ነፃ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ለተጨማሪ ምክክር ምንም መክፈል አይጠበቅብዎትም። በአንዳንድ ማዕከላት የምክር አገልግሎት በተለያዩ ቋንቋዎች ይሰጣሉ።

አጠቃላይ የምክር አገልግሎት ማዕከላት

የስደተኞች ማዕከላዊ ምክር አገልግሎት ማእከላት፣

  • GGG Migration
    GGG የስደተኞች ማዕከል ሰራተኞች በስዊዘርላንድ ውስጥ ከዕለት ተዕለት ኑሮ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ በተለያዩ 14 ቋንቋዎች ጥያቄዎችን በሚመለከት መልስ ይሰጣሉ። ምናልባት የጀርመን ኮርስ ወይም የውህደት ኮርስ አቅርቦት በመፈለግ ላይ ሊሆኑ ይችላል። የGGG የስደተኞች ማዕከል ሰራተኞች በዚህ ይረዱዎታል። የምክር አገልግሎቱ በስልክ ወይም በአካል ነው። በተቻለ መጠን አስቀድመው ቢመዘገቡ ጥሩ ነው። ምንም ዓይነት ክፍያ መክፈል የለብዎትም።

ስለ የጥገኝነት እና ለውጭ ዜጋዎች የኢሚግሬሽን ህግ መረጃ፡-

  • BAS Beratungsstelle
  • Freiplatzaktion

ሌሎች ተጨማሪ የምክር አገልግሎት ማዕከላት፣

  • አጠቃላይ የምክር አገልግሎት የሚያገኙባቸው ተጨማሪ የምክር ማዕከላት አሉ። አንዳንድ ቢሮዎች ከጀርመንኛ ሌላ በሌላ ቋንቋ ያማክሩዎታል።
  • ከስደተኞች ማህበራት አጠቃላይ መረጃ በራስዎ ቋንቋ ማግኘት ይችላሉ።

የካንቶን አስተዳደር ጽ/ቤት / የማዘጋጃ ቤት የኮምዩኑ አስተዳደር ጽ/ቤት (DE)

ብዙውን ጊዜ በሚኖሩበት ቦታ ያሉ የአስተዳደር ጽ/ቤቶች ሊያግዝዎት ይችላሉ፣ ለምሳሌ የካንቶን አስተዳደር ጽ/ቤት ወይም የማዘጋጃ ቤት የኮምዩን አስተዳደር ጽ/ቤት። የጽ/ቤቱ ሰራተኞች ለጥያቄዎችዎ መልስ ሊሰጡዎት ይችላሉ። ወይም የትኛው የምክር ማእከል ሊረዳዎት እንደሚችል ሊጠቁምዎት ይችላሉ። በጽ/ቤቶቹ ድረ-ገጾች ላይ የስልክ ቁጥሮችን፣ የኢሜል አድራሻዎችን፣ የመክፈቻ ጊዜዎችን እና ሌሎች መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።

የልዩ ምክር አገልግሎት ሰጪ ማዕከላት

በባዝል ክልል ውስጥ በአንድ የተወሰነ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ምክር የሚሰጡ ብዙ የምክር አገልግሎት ማዕከሎች አሉ። ለምሳሌ፡- ስለ ዕድሜ፣ ሥራ፣ የመኖሪያ ፈቃድ፣ ትምህርት፣ ጋብቻ/ፍቺ፣ አስተዳደግ፣ ቤተሰብ፣ ፋይናንስ (ዕዳ/በጀት)፣ ጤና፣ የቤት ውስጥ ጥቃት፣ ከህብረተሰቡ ጋር ውህደት፣ ሥነ ልቦናዊ ችግሮች፣ ሕፃናትን መንከባከብ፣ እርግዝና፣ ጾታዊ ችግር፣ ሱስ፣ ማህበራዊ ጉዳዮችን ይመለክታሉ። ብዙውን ጊዜ ለመጀመሪያው የምክር አገልግሎት ግዜ መክፈል የለብዎትም። የአንዳንድ የምክር አገልግሎት ማዕከላት አድራሻ በ "ሄሎ ባዝል-ከተማ" "Hallo Basel-Stadt". በማውጫው ላይ ባለው ርዕስ ስር ያገኛሉ። ወይም የመረጃ እና የ GGG የምክር አገልግሎት ማእከል GGG Migration ሰራተኞችን ይጠይቁ። ሰራተኞቹ የተለያዩ ብዙ ቋንቋዎችን ይናገራሉ እና ለጥያቄዎ ተስማሚ የሆነ የምክር አገልግሎት አቅርቦቶች መረጃ ይሰጥዎታል።

ገና ጀርመንኛ በደንብ መናገር አይችሉም? የማይችሉ ከሆነ ከምክር አገልግሎት ማእከሉ አስተርጓሚ ያስፈልግዎታል። ወደዚያ ከመሄድዎ በፊት የምክር አገልግሎት ማእከሉን ይጠይቁ። አንዳንድ የምክር አገልግሎት ማዕከላት በሌሎች ቋንቋዎች የምክር አገልግሎት ሊሰጡዎት ይችላሉ። ወይም ማዕከሉ ሊተረጉምሎት የሚችል ተርጓሚ ሊያዘጋጁሎት ይችላሉ። ምናልባትም የሚተረጉምልዎትን ሰው ይዘው መምጣት ያስፈልጎት ይሆናል።

የዘር መድልዎ

አድልዎ ወይም ዘረኝነት አጋጥሞዎታል? ወይስ አድልዎ ወይም ዘረኝነትን ታዝበዋል? የምክር አገልግሎት የሚሰጡ ማዕከላት አሉ፡-

  • "ዘረኝነት ይቁም" "STOPP Rassismus" ለባዝል-ከተማ እና ለባዝል-ላንድሻፍት ካንቶኖች የምክር አገልግሎት ማእከል ነው። ውይይቱ ነፃ አስተማማኝ እና ሚስጥራዊ ነው። በስልክ፣ በአካል ወይም በኦን ላይን በመስመር ላይ ምክር ማግኘት ይችላሉ።
  • ዘረኝነት ወይም መድልዎ ካጋጠመዎት "የፀረ-ዘረኝነት አውታረ መረብ" "Netzwerk Antirassismus" ይደግፈዎታል።
  • የ"GRA ፋውንዴሽን" "Stiftung GRA" ፀረ-ሴሚቲክ አድልዎ ላይ የምክር አገልግሎት ይሰጣል።