የጤንነት ስርዓት

በስዊዘርላንድ ያለው የጤና አጠባበቅ ሥርዓት በጣም የዳበረ ነው። ሁሉም ነዋሪዎች በአደጋ እና በህመም ላይ አጠቃላይ እና የግዴታ ዋስትናና ኢንሹራስ አላቸው። ብዙ የሕክምና ጣብያዎች፣ መድሃኒት ቤት እና ሆስፒታሎች አቅርቦቱን ያረጋግጣሉ።

የኢንሹራንስ ስርዓት

በስዊዘርላንድ ሁሉም ነዋሪዎች ከአደጋ እና ከበሽታ ለመጠበቅ ሁሉም ኢንሹራንስ አላቸው። ወደዚህ አገር አዲስ የመጣ ማንኛውም ሰው ከገባ በኋላ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ውስጥ ኢንሹራንስ መግባት አለበት። ልጆች ከተወለዱ በሦስት ወር ውስጥ ኢንሹራንስ መግባት አለበት። የግዴታ ኢንሹራንስ ጥቅሞች በሕግ የተደነገጉ ናቸው። ሁሉም የመድን ዋስትና ወይም ኢንሹራንስ ያላቸው ሰዎች አንድ ዓይነት የሕክምና አገልግሎት የማግኘት መብት አላቸው።

ፋይናንስ ማድረግ

የስዊዘርላንድ የጤና አጠባበቅ ስርዓት በመንግስት (የፌዴራል መንግስት፣ ካንቶኖች፣ የኮሙን ማዘጋጃ ቤቶች)፣ እና በግለሰቦች በጋራ በመተባበር ፋይናንስ የሚደርግ የሚሸፈን እና ፋናንስ የሚደረግ ነው። ግለሰቦች ለጤና መድን እና ለአደጋ መድን ወርሃዊ የኢንሹራንስ ድርሻቸውን ይከፍላሉ። ይህ በየአመቱ የሚዘጋጅ ሆኖ ከካንቶን ወደ ካንቶን ይለያያል። ማንኛውም ሰው ቢታመመ ወይም አደጋ ቢያጋጠመው ህክምና ወጪው (Franchise und Selbstbehalt) በመዋጮው መጋራት አለበት። ይሁን እንጂ ክፍያው ወይም ወጪው በዓመቱ ቢበዛ ከፍተኛ የክፍያ መጠን አለው ።

የጽሑፍ ትርጉሞች

በውጭ ቋንቋ ከዶክተሮች፣ ፋርማሲስቶች ወይም ነርሶች ጋር መነጋገር በሚኖርበት ጊዜ ቀላል አይደለም። ስለዚህ አንዳንድ ሆስፒታሎች በልዩ የሰለጠኑ የባህል ተርጓሚዎች ነፃ ትርጉም ይሰጣሉ። ታካሚዎች ስለዚህ ጉዳይ እራሳቸውን አስቀድመው ማሳወቅ አለባቸው። ተርጓሚዎቹ ለዶክተር ወይም ለሌሎች ሁኔታዎች ጉብኝት ሊታዘዙ ወይም ሊቀጠሩ ወይም ሊጠሩ ይችላሉ። ግን ታድያ ሂሳቡን በራስዎ መክፈል አለብዎት።