የህክምና እና የአደጋ ኢንሹራንስ

በስዊዘርላንድ ውስጥ የሚኖር ማንኛውም ሰው የአደጋ እና የጤና መድን ኢንሹራንስ ሊኖረው ይገባል። እነዚህ የግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች በአደጋ፣ በህመም ወይም በእርግዝና ወቅት ወጪዎችን ይሸፍናሉ። ሁለቱም ዓይነት ኢንሹራንስዎች ወደ አገሪቱ ከገቡ በኋላ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ባሉት ጊዜዎች ውስጥ መገባት

የጤና እንክብካቤ ኢንሹራንስ (መሰረታዊ ኢንሹራንስ)

ሁሉም የስዊዘርላንድ ነዋሪዎች የጤና መድህን (መሰረታዊ ኢንሹራንስ፣ Grundversicherung) ራሳቸው የግድ መግባት አለባቸው። ወደ ስዊዘርላንድ ለመኖር አገር የሚቀይር ማንኛውም ሰው ይህን ለማድረግ ሦስት ወር አለው። በዚህ ጊዜ ውስጥ አንድ ሰው ቢታመም፣ ቢሆንም እንኳን ይሸፈናሉ። መሰረታዊ ኢንሹራንስ በብዙ የግል የጤና መድን አገልግሎት ሰጪዎች (Krankenkassen) ይሰጣል። የጤና ኢንሹራንስ ኩባንያዎን ለመምረጥ ነፃ ነዎት። የጤና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች በስዊዘርላንድ የሚኖሩትን ሁሉ የመቀበል ግዴታ አለባቸው።

ኢንሹራንስ የገባ ሰው በየወሩ መክፈልል የሚገባውን ሂሳብ ይከፍላል። እነዚህ ፕሪሚየሞች እንደ ጤና ኢንሹራንስ ኩባንያ እና እንደ ኢንሹራንስ ሞዴል ይለያያሉ። ስለዚህ ቅናሾቹን ማወዳደር ጠቃሚ ነው። ለሚቀጥለው ዓመት እስከ ህዳር መጨረሻ ድረስ የጤና መድን መቀየር ይችላሉ። መሰረታዊ ኢንሹራንስ ከታመሙ ወጪዎችን ብቻ ሳይሆን በእርግዝና እና ልጅ በመውለድ ጊዜም ጭምር ይከፍላል። የሚሰጡት አገልግሎቶች (ጥቅሞቹ) በሕግ የተደነገጉ ናቸው::

ማሳሰብያ፡ ለጥርስ ህክምና ወይም የመነጽር ወጪዎች አብዛኛውን ጊዜ በራስዎ መከፈል ወይም በፈቃደኝነት ተጨማሪ ኢንሹራንስ መግባት አለብዎት።

የአደጋ ግዜ ኢንሹራንስ

ሰራተኞች በሳምንት ውስጥ ከ 8 ሰአታት በላይ የሚሰሩ ከሆነ በስራ ወቅት ለሚደርሱ አደጋዎች እና ነፃ ጊዜ በአሰሪው የኢንሹራንስ ዋስትና ይሰጣቸዋል። አነስተኛ ስራ የሚሰሩ ሰዎች በትርፍ ጊዜያቸው ለአደጋ ዋስትና ወይም ኢንሹራንስ አይኖራቸውም እና በራሳቸውን የአደጋ ኢንሹራንስ መግባት አለባቸው። ይህ በግል ስራ የሚተዳደሩ እና ለሰራተኞች እና ስራ ለሌላቸው ሰዎች ሁሉም ይሠራል። ያልተቀጠሩ ሰዎች ከጤና ኢንሹራንስ ኩባንያቸው ጋር የአደጋ ኢንሹራንስ መውሰድ አለባቸው። የግል ተቀጣሪው ከሌሎች የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ጋር የአደጋ ኢንሹራንስ ሊወስድ ይችላል። የኢንሹራንሱ ክፍያ በየወሩ መክፈል ይኖርበታል። በሠራተኞች ላይ፣ በቀጥታ ከደመወዛቸው ላይ ይቀነሳሉ።

የፕሪሚየም ቅነሳ

የጤና መድህን ፕሪሚየም መግባት የማይችሉ ሰዎች ለመሠረታዊ ኢንሹራንስ የፕሪሚየም ቅናሽ (Prämienverbilligung) ሊያገኙ ይችላሉ። ፕረምየም ለመቀበል አንድ ሰው የማመልከቻ ቅጽ ማቅረብ እና በንብረቶች እና ገቢዎች ላይ መረጃ መስጠት አለበት። ማመልከቻው ተቀባይነት ካገኘ፣ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ፕረምየም ክፍያዎችን መክፈል ይጀምራል። የማህበራዊ መዋጮ ቢሮ (Amt für Sozialbeiträge) ስለ ፕረምየም ቅነሳ መረጃ ያቀርባል እና ምዝገባውን ይጀምራል።

ከመሠረታዊ ኢንሹራንስ ላይ ሌላ ተጨማሪ ተጨማሪ ኢንሹራንስ

በግዴታ መገባት ካለባቸው መሰረታዊ ኢንሹራንስ በተጨማሪ የተለያዩ ማሟያ ኢንሹራንሶች (Zusatzversicherungen) በፈቃደኝነት መግባት ይችላሉ። እነዚህ በመሠረታዊ ኢንሹራንስ ያልተሸፈኑ እንደ የጥርስ ህክምና ያሉ ጥቅማ ጥቅሞችን ይሸፍናሉ። ተጨማሪ ኢንሹራንስ በሁሉም የጤና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ይሰጣል። የጤና ኢንሹራንስ ኩባንያዎቹ ለአንድ ሰው ኢንሹራንስ እንዲገባ ለመቀበል ወይም ላለመቀበል በራሳቸው ሊወስኑ ይችላሉ እንዲሁም ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታዎችን ማስቀመጥ ይችላሉ።