የዲፕሎማ ዕውቅና

የውጭ አገር ዲፕሎማዎች እና ዲግሪዎች በስዊዘርላንድ ውስጥ ሁልጊዜ ተቀባይነት አያገኙም። እንደየሁኔታው ግን ዲፕሎማውን እውቅና ማግኘት ይቻላል። ይህ ለአንዳንድ የሙያዎ ዘርፎች ግን ግዴታ ነው።

ዕውቅና

የውጭ አገር ዲፕሎማ ያላቸው ሰዎች በተወሰኑ ሁኔታዎች በስዊዘርላንድ ውስጥ እውቅና ሊያገኙ ይችላሉ። እውቅናው የውጭ አገር ዲፕሎማው ወይም ዲግሪው ከስዊዘርላንድ ዲፕሎማ ወይም ዲግሪ ጋር እኩል መሆኑን ያረጋግጣል።.ቁጥጥር የሚደረግባቸው ሙያዎች (ለምሳሌ የነርሲንግ ባለሙያዎች፣ መምህራን፣ ወዘተ) ከሆነ በሙያውን ለመስራት የግድ ዕውቅና ያስፈልጋል። ለዕውቅናው እንደ ሙያው ወይም እንደ ትምህርቱ ዓይነት የተለያዩ አካላት እውቅና ይሰጣሉ።ለእውቅናውም ክፍያ ይከፈላል።. የብሔራዊ የዲፕሎማና የዲግሪ ዕውቅና ማዕከል (Nationale Kontaktstelle für Diplomanerkennung) ወይም ከሙያ፣ ጥናትና የሥራ አማካሪ አገልግሎት (Berufs-, Studien- und Laufbahnberatung) መረጃ ማግኘት ይቻላል።

ደረጃ ማረጋገጥ

ቁጥጥር የማይደረግባቸው ሙያዎች ጋር በተያያዘ በስዊዘርላንድ ውስጥ ለመስራት የዲፕሎማ ወይም የብቃት ማረጋገጫ እውቅና አያስፈልግም። ለእነዚህ ሙያዎች የደረጃ ማረጋገጫ (Niveaubestätigung) ማመልከት ይችላል። ይህ የሚያሳየው የውጭ አገር ዲፕሎማ ስዊዘርላንድ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ያለውን ዋጋና ግምት ነው። ማረጋገጫው ሥራ ሲፈልጉ ሊረዳ ይችላል። ደረጃውን ስለማረጋገጥ መረጃ ከብሔራዊ የመገናኛ ነጥብ ለዲፕሎማ ዕውቅና ወይም ከስራ፣ ከጥናት እና ከሙያ ምክር አገልግሎት አገልግሎት ጽ/ቤት (Berufs-, Studien- und Laufbahnberatung) ማግኘት ይቻላል።

የሙያ ብቃትን በኋላ ማሟላት

ሙያዊ ልምድ ያላቸው ነገር ግን እውቅና ያለው ዲፕሎማ ወይም እውቅና ያለው ብቃት ማረጋገጫ የሌላቸውና ያልተመረቁ አዋቂዎች የስዊስ መመዘኛዎችን የሚያሟላ መሰረታዊ የሙያ ስልጠና ወይም ከፍተኛ የሙያ ስልጠና ማድረግ ይችላሉ። የአሰራር ሂደቱ በቀድሞው ትምህርታቸው፣ በሙያዊ ልምዳቸው እና በእድሜያቸው ላይ የተመሰረተ ነው። ያም ሆነ ይህ፣ በቂ የጀርመንኛ እውቀት መኖር ዋና መስፈርት ነው (ደረጃ B1/B2 በGER መሠረት)። ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ከሙያ፣ ጥናት እና የስራ አማካሪ አገልግሎት ጽ/ቤት (Berufs-, Studien- und Laufbahnberatung) በነጻ መረጃ እና ምክር ማግኘት ይችላሉ። የሙያ ብቃትን ተምሮ ያሟላ ማንኛውም ሰው በስራ ገበያው ላይ ያለውን እድል ያሻሽላል እና ተጨማሪ ስልጠና የማግኘት እድልም ይኖረዋል።