የመንጃ ፍቃድ

በስዊዘርላንድ ውስጥ መኪና ወይም ሞተር ሳይክል ለመንዳት ሕጋዊ የመንጃ ፍቃድ ያስፈልግዎታል። ወደ ስዊዘርላንድ ከመጡ በኋላ የውጭ አገር የመንጃ ፈቃዶች መቀየር አለባቸው።

የውጭ አገር መንጃ ፍቃድ

ወደ ስዊዘርላንድ የሚመጣ ሰው እና መንጃ ፍቃድ ያለው ማንኛውም ሰው በ12 ወራት ውስጥ ወደ ስዊዘርላንድ መንጃ ፍቃድ (Führerausweis) ማስቀየር አለበት። ይህንን ለማድረግ በ Basel-Stadt የሞተር ተሽከርካሪ መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት (Motorfahrzeugkontrolle) ማመልከቻ ማቅረብ አለበት። የመንጃ ፈቃዱ እንደወጣበት አገር ይለያያል፣ ለመለወጥ እንደሁኔታው የተለያዩ ደንቦች ተፈጻሚ ይሆናሉ። የፍተሻ መንዳት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፣ ወይም ነጂው /አመልካቹ/ የስዊስ ቲዎሪ ፈተናን ማለፍ አለበት። ይህንን በሚመለከት የባዝል-ከተማ Basel-Stadt የሞተር ተሽከርካሪ መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ተጨማሪ መረጃ ይሰጣል።.

የመንዳት ፈተና

በስዊዘርላንድ የመንጃ ፍቃድ ለማግኘት፣ ፈተና አስፈላጊ ነው። የመንዳት ፈተናው የንድፈ ሃሳባዊ እና ተግባራዊ ክፍልን ያካትታል። ከ17 አመት በላይ የሆኑ ሰዎች ብቻ ፈተናውን እንዲወስዱ ይፈቀላቸዋል። የሞተር ተሽከርካሪ መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ስለ መስፈርቶቹ እና ስለ ትክክለኛው አሰራር መረጃ ይሰጣል። ለጭነት መኪናዎች፣ አውቶቡሶች እና ታክሲዎች ለማሽከርከር ልዩ ፈተናዎች ያስፈልጋሉ።